ሌሶ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ ፋብሪካ አስመረቀ

Date:



በኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት ምርት ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው የተባለለትን ከፍተኛ ጥራት ያለውን ፋብሪካ በሱሉልታ ክፍለ ከተማ ተመርቋል።

ሌሶ ኢትዮጵያ በሸገር ከተማ ያቋቋመው ፋብሪካ የአገር ውስጥ ምርት ለማጠንከር እና ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የውጪ ምርቶች ላይ ጥገኝነት ይቀንሳል መባሉን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

ሌሶ ኢትዮጵያ በ 2009 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን ለውሃ ማስተላለፊያ፣ ለቆሻሻ ማስወገጃ እና የኤለክትሪክ መስመሮችን ለመዘርጋት የሚያገለግሉ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የቧንቧዎች እጥረትን ለመቅረፍ የተቋቋመው ሌሶ ትልልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች አስተማማኝ ምርቶችን በማቅረብ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል።

እ.ኤ.አ ከ2016 ጀምሮ የቻይናው ሌሶ ግሩፕ ሆልዲንግ ሊሚትድ ብቸኛ ወኪል የሆነው ኩባንያው ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎች እና የቴክኖሎጂ እድገቶች በኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት እንዲጣመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።

በሸገር ከተማ የተቋቋመው አዲሱ ፋብሪካ  በውጭ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ፣ የውጭ ምንዛሬን ለመቆጠብ የታለመ ስትራቴጂያዊ ኢንቨስትመንት መሆኑን ብስራት ሰምቷል። ተቋሙ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የመሰረተ ልማት ምርቶችን የማምረት አቅሟን ከማሳደግ ባሻገር ለምህንድስና ባለሙያዎች እና ለኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ስልጠና እና ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል።

ሌሶ ኢትዮጵያ የግብርና ምርቶች ወደ ውጭ የሚልክ ሲሆን ከጉጂ በሚያቀርበው “ዳዋ” የተሰኘው የቡና ምርት አማካኝነት ኩባንያው የኢትዮጵያን ከፍተኛ ጥራት ያለው ቡና ወደ እስያ እና መካከለኛው ምስራቅ በመላክ ለኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተቋሙ ገልጿል።

ሱሉልታ ላይ በተደረገው የፋብሪካው የምርቃት ስነ-ስርዓት የመንግስት ባለስልጣናት፣ የቦርድ አባላት፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች እና ነጋዴዎች ተገኝተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...

ሕወሓት ድብረጺዮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

የክልሉ ፕሬዚዳንት ተደርገው የተመረጡት  ድብርጺዮን ገ/ ሚካዔል (ዶ/ር)  ቃለ...

” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” – ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ...

የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም

የጥንት ኢትዮጵያዊያንአርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ ሚያዚያ...