በጥናት መሰረት ለህንፃ ቤተ መቅደስ እድሳት 150 ሚሊዮን ብር ጠይቋል ለተባለው መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡
ቤተ ክርስቲያኑ ጣሪያው በመዛጉና በመቀደዱ፣ በግቢው የሚገኙ የዛፍ ሥሮች በህጻው መሰረት በመግባታቸው የተለያዩ ጉዳቶች ደርሰውበታል ተብሏል።
እንዲሁም ጣሪያው ዝናብ እያፈሰሰ በመሆኑ ግድግዳ እንደተሰነጠቀና የግቢው መሬት በመንሸራተቱ ሕንጻው አስቸኳይ እድሳት እንደሚያሻው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ያስታወቀው ኮሚቴው፣ ቅዱስ ሲኖዶስና ከተማ አስተዳደሩ ህንጻው ታሪኩን በጠበቀ መልኩ እድሳት እንዲደረግለት መፍቀዳቸውን አስረድቷል፡፡
ባለሙያዎች ለሦስት ወራት አደረጉት በተባለ ጥናት መሰረት ለህንጻ ቤተ ክርስቲያኑ እድሳት ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ፣ 126 ሚሊዮን ዝቅተኛ ዋጋ አቅርቦ ጨረታውን ያሸነፈው ሚሳክ ጄኔራል ኮንስትራክሽን ሥራውን ተረክቦ እየሰራ እንደሚገኝም ተመልክቷል፡፡
በመሆኑም መላው ኢትዮጵያውያንና የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ታሪካዊ ቅርሱን ለማዳን እገዛ እንዲያደርጉ፣ ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል፡፡
“መላው ኢትዮጵያውያን፣ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች፣ የሚዲያ ተቋማትና ጋዜጠኞች ይህንን ታሪካዊ ቅርስ ለማዳን እገዛ እንዲያደርጉ” ሲል ጥሪ ያቀረበው ኮሚቴው፣ “ሁሉም ኢትዮጵያውያን የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው፣ በሀሳብ፣ በሙያ እና በጸሎት ኮሚቴውን እንዲያግዙ” ሲልም ጠይቋል።
(ድጋፍ ማድረጊያ የባንክ ሁሳብ ቁጥሮች ከታች ተያይዛል)
የንግድ ባንክ 1423
ዓባይ ባንክ 1423 (9142110956864727)
ዳሸን ባንክ 1423
አማራ ባንክ 1423
አቢሲንያ ባንክ 1423
ንብ ባንክ 1423 (7000100492127)
አዋሽ ባንክ 013201167911100
Coop 1423 (1050900119942)
አንበሳ ባንክ1423 (30712777708)
ፀሐይ ባንክ 1423 (1007093857)
