ቻይና ጃፓንን ያሸነፈችበት 80ኛ ዓመት የድል በዓል እና የሁለተኛው ጦርነት ማብቂያ በነገው በታላቅ ወታደራዊ ትርኢት እያከበረች ትገኛለች።
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢምፒግ የድል ቀኑን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር “ቤጂንግ የትኛውንም ሀይል አትፈራም፤ አትበገርም ሁሌም ከፊት ትቀድማለች” ሲሉ አበክረው ተናግረዋል።
በቤጂንግ አደባባይ እየተከበረ በሚገኘው በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ የ26 ሀገራት መሪዎች ታድመዋል።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጨምሮ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በወታደራዊ ክብረበአሉ ከተገኙት መካከል ይጠቀሳሉ።
ዢ ፣ ፑቲንና፣ ኪም በአንድ ላይ ሲገናኙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነውም ተብሏል ።
እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ግዙፍ ወታደራዊ ትርኢት ላይ ቻይና አዳዲስ የሀይፐር ሶኒክ ሚሳኤልች ጨምሮ፣ ሰው አልባ የባህር ውስጥ ድሮኖችና ተዋጊ ጄቶች ለአለም ታሳያለች ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህም ባሻገር ቤጂንግ ለምዕራባውያን በርካታ መልዕክቶችን አሳልፉበት የሚጠናቀቅ መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል ሲሉ ተንታኞች ገልፀዋል ።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
