የጷጉሜ ቀናት የተሰጣቸውን ስያሜና መሪ ሃሳብ መነሻ በማድረግ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎችና መንግሥታዊ መዋቅሮች በድምቀት እንደሚከበሩ የኢፌዴሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ለመገናኛ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኢትዮጵያ የራሷ የዘመን አቆጣጠር፣ ጥንታዊ ታሪኮችና ቅርሶች ባለቤት ናት ብለዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ ልዩው 13ኛ ወር ጷጉሜ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎችና መንግሥታዊ መዋቅሮች ይከበራል ሲሉ ገልጸዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት እነኝህን ወደሀብት በመቀየር የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ኢትዮጵያን ከድህነት ለማላቀቅ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል።
በዚህም የ2017 ዓ.ም የጷጉሜ ቀናት ሲያሜዎቻቸውና የሚከበሩባቸው መሪ ሃሳብ ይፋ አድርገዋል። በዚሁ መሠረትም፤
ጷጉሜ 1 – የፅናት ቀን – “ፅኑ መሠረት ብርቱ ሀገር “
ጷጉሜ 2 – የህብር ቀን – “ብዘሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ”
ጷጉሜ 3 – የዕምርታ ቀን – “ዕምርታ ለዘላቂ ከፍታ”
ጷጉሜ 4 – የማንሰራራት ቀን – “ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት”
ጷጉሜ 5 – የነገው ቀን ሆነው በመላ ሀገሪቱ እንደሚከበር ተናግረዋል።
ጋዜጣ_ፕላስ
