ሜድ ኢድ አፍሪካ 2026 ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነዉ

Date:

በአፍሪካ የጤናውን ዘርፍ አቅም ለማጎልበትና ትብብርን ለመፍጠር ያለመው “ሜድ ኢድ አፍሪካ 2026” (MED ED AFRICA 2026) ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከሰኔ 29 እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም (July 6-8, 2026) በአዲስ አበባ ከተማ ለሦስት ቀናት እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በመድረኩ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የተወከሉ የጤና ሚኒስትሮች፣ የፖሊሲ አውጪዎች፣ አካዳሚካውያን፣ ተመራማሪዎችና የዘርፉ አጋሮችን ጨምሮ ከ800 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል።

“Preparing Africa’s Health Workforce for an Uncertain Future” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ ጉባኤ፤ የአመራር ብቃትን ማጠናከር፣ ቴክኖሎጂና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) ከሕክምና ትምህርት ጋር ማቀናጀት፣ የእናቶችና ሕፃናትን ጤና ጨምሮ ጤናማ አፍሪካን መገንባት፣ እንዲሁም የሴቶችን የውሳኔ ሰጪነት ሚና ማሳደግ በሚሉ አራት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ያተኩራል።

ጉባኤውን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ከኮምሳ (COMSA) እና ከግሎባል ሄልዝ ኢኩዊቲ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን በዋና አዘጋጅነት የሚመራው ሲሆን፣ በሦስቱ ቀናት የምርምር ሥራዎችና ከ15 በላይ ድርጅቶች የሚሳተፉበት ኤግዚቢሽን ይካሄድበታል።

ኢትዮጵያ መድረኩን ማስተናገዷ በሕክምና ትምህርትና ልዩ ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ ያላትን ተሞክሮ ለማካፈል፣ የቱሪዝም ዘርፉንና ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት፣ እንዲሁም የአገሪቱን ገጽታ ለመገንባት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ጤና ሚኒስቴር አመልክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዜጋዬ ተገድሏል ያለችው ጋና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገባች

አንድ ጋናዊ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ካለው ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ...

«የማይናገረው ልዑል» መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ ነው

ደራሲ መሠረት ክንፈ ኃይሌ ከኦቲዝም ጋር ከሚኖረው ልጇ ልዑል...

በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚደረግ ንግድ በገንዘብ መጠን ተገደበ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚከናወነውን...

(IMF) ከ460 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አፀደቀ

አዳዲስ ብድር በመውሰድ ረገድ ጥንቃቄ እንድታደርግ ኢትዮጵያን ያስጠነቀቀው IMF...