ስለ ማይግሬን ማወቅ ያለባች

Date:

እንደ ማይግሬን ያሉ የነርቭ በሽታዎች በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጤና መታወክ ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው ተብሏል።

ማይግሪን ከባድ የራስ ምታት ብቻ ሳይሆን የብዙ በሽታዎች ምልክት ሊሆን የሚችል የነርቭ በሽታ ሲሆን ብዙውን ጊዜ በቤሰተብ ጭምር የሚመጣ እና በሁሉም የዕድሜ ክልሎች ላይ ሊከሰት የሚችል ነው።

በአብዛኛውን በአንድ ጎን የጭንቅላት ክፍል ላይ የሚከሰት ሲሆን ማቅለሽለሽ፣ ለብርሃን እና ለድምጽ ስስ መሆን አብሮት ይመጣል።

🔔ማይግሪን አራት ደረጃዎች አሉት።

  1. ድሮም (Prodrome) – የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች (የስሜት ለውጦች፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ድካም) ህመም ከመጀመሩ በፊት ከ24 እስከ 48 ሰዓታት ድረስ ይቆያል።
  2. ኦራ(Aura) – ከራስ ምታት በፊት አብሮ የሚሄድ የእይታ ወይም የስሜት መረበሽ የሚከሰትበት ነው።
  3. ራስ ምታት(Headache) – ዋናው የህመም ደረጃ ሲሆን ከሰዓታት እስከ ቀናት የሚቆይ ነው።
  4. ድህረ-ድሮም (Postdrome) – ህመሙ ከቀነሰ በኋላ የሚቆይ ድካም፣ ትኩረትን የመሰብሰብ ችግር የሚከሰትበት ነው።

በማይግሬን ከአለም ህዝብ 12 በመቶ ያህሉ ይጠቃል የተባለ ሲሆን በሴቶች ላይ በብዛትይከሳታል፡፡

⁉️ለማይግሪን እንደ መነሻ ምክንያቶች የሚጠቀሱት ምንድናቸው?

ቀስቃሽ ምክንያቶቹ ከሰው ወደ ሰው ቢለያዩም፣ የተለመዱ የሚባሉት ፡-

✔️ጭንቀት ፡- 80 በመቶ የሚሆኑ ታማሚዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።
✔️የሆርሞኖች መለዋወጥ (ለምሳሌ የወር አበባ ዑደት፣ እርግዝና)
✔️የምግብን ሰዓትን መዝለል፣ እንቅልፍ ማጣት፣ የአየር ሁኔታ ለውጥ እና ጠንካራ ሽታ ያላቸው ነገሮች እንደምክንያት ይጠቀሳሉ ተብሏል።

የአኗኗር ዘይቤን ማሻሻል ፣ የማይግሬን የሚከሰትበትን ጊዜ በማስታወሻ ደብተር መያዝ፣ እንቅልፍን ማስተካከል ፣ ጭንቀትን መቀነስ፣ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እና የታወቁ ቀስቃሽ ነገሮችን ማስወገድ መፍትሔ ሊሆን ይችላል ይላል ከናሽናል ላይብረሪ ኦፍ ሜዲስን የተገኘው መረጃ፡፡ ጤናዎን ይጠብቁ!

ሸገርኤፍኤም102_1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...