በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘንድሮው ዓመት 5 ሚሊዮን የወተት ላሞች በሰው ሠራሽ ሥነ ዘዴና በመደበኛ መንገድ ለማዳቀል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ አስታውቀዋል።
ይህ እንቅስቃሴ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርን ለማሳካት፣ በምግብ ራስን ለመቻልና ስርዓተ ምግብን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እያበረከተ ነው ብለዋል።
በዶሮና በንብ ዕርባታ ላይም አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ሚኒስትር ዲኤታው፤ በዘንድሮው ዓመት በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በምዕራብ አርሲ ዞን በሰው ሠራሽ ሥነ ዘዴ የማዳቀል ሥራ መጀመሩ የዕቅዳችን አንዱ አካል ነው ብለዋል።
