” ስም ያለው ሞኝ ነው” ፤ የማለዳው የስድብ ውርጅብኝ‼️

Date:

📍ጽንፍ የረገጠ ክብረ- ነክ ስድብና ዘለፋ አይበጀንም ‼️
📍” አንተ ነብዩ ነህ አይደል ? ” ‼️

ሐሙስ ማለዳ ከእንቅልፍ አንድ የስልክ ጥሪ ቀሰቀሰኝ … ስልኬን አነሳሁና … ሃሎ ማን ልበል … አልኩ ። የማላውቀው ደዋዩ ጎርነን ያለ ድምጽ ያለው እድሜ ጠገብ ይመስለኛል። ንግግሩን በቀጥታ ቀጠለ …
📞” አንተ ነብዩ ነህ አይደል ? ” አለኝ ።
🎙 አዎ እንዳልኩት ከፊት ለፊቴ መጥቶና አንገቴን ፈጥርቆ በገነገነ ጥላቻ ምራቁን ፊቴ ላይ እየተፋ በሚመስል ስሜት የስድብ መአቱን ያወርድብኝ ገባ … ” በዚህ ልክ የሚጠላኝ አለ ወይ እስክል …ዳሩ ግን ስድብ ቢደግሙት ያው ስድብ ነውና እሱ ባንደበቱ ያለውን እኔ በዚህች ማስታወሻ ጽሁፌ አልድገመው… በስድቡ መካከል ጣልቃ ገብቼ…

🎙 ለመሆኑ በጠዋት ደውለህ በዚህ ልክ የምትዘልፈኝ ምን ጥፋት አጠፋሁ ? ስል ደዋዩ ወደ ራሱ እንዲመለስና ጥፋት ካጠፋሁ እንደሚነግረኝ ለማረጋጋት እየሞከርኩ ጠየቅኩት …

📞” ለሆድህ ሳይሆን ለህሊናህ ኑር ብላቴናው ቴዲ ንጉሥ ነው ። ” ብሎ ስልኩን ከላዬ ላይ ዘጋው…ቀጣይ ምላሹ የከፋ ሆነ…

📍 ስልኩን ዘግቸ ብዙ ክፉ ደጉን አውግቸ አወረድኩት …
ላፍታ የሆነውን እያስታወስኩ ቆዘምኩ … ከተሳዳቢው በላይ ያመመኝ ያለ ስራዬና ግብሬ ስልኬ ሆን ብሎ የሰጠውን ያ ክፉ ሰው ማን ይሆን ? ብዬ ከእራሴ ጋር ሙግት ይዣለሁ 😪 ዳሩ ግን ” ስም ያለው ሞኝ ነው ” ሆኖ ለሌላ የተተኮሰው በስመ መኩሼው በእኔ ላይ ቢደርስም አስደንጋጭ እና ልብ ሰባሪ የሆኑ ስድቦቹ ለእኔ የተላኩ ባይሆንም ነፍሴ ስለ ተሰዳቢው ሰው ተከፋች … የሰው ልጅ በጥበብ ተራቆ ሰላምና ፍቅርን ከሚገልጽበት በላይ ልብን ለሚሰብር ስድብም በዚህ ደረጃ የተራቀቅን መሆኑን ሳስብ ከምር ጊዜውን ሳይሆን ሰውነታችን ሲጎዳ በዚህ ደረጃ መርዝ የሚመንጨቱን ልክ ፈራሁት ….

🎯 ዛሬ የዘመኔ የሙዚቃ ንጉሥ የብላቴናው የቴውድሮ ካሳሁን ገርማሜ 🎤 ኢቶሪካ 🎼 ETORIKA 🥁 ዛሬ 18-8-8-8 🕗 ይለቀቃል ። ቴዲ አፍሮ በጉጉት ስጠብቀው ንጉሡን ንጉሥ ከሚል ሰው የተሰነዘረውን ክብረ ነክ ስድብ እየሰቀጠጠኝም ቢሆን ችሎ ማለፍ ግድ ብሎኛል ። ዳሩ ግን በሰላም በፍቅርና በህብራዊ ሙዚቃው ቴዲን የሚያነግሱ ወገኖች ስሜትን የሚጎዳ ምንም ነገር እንኳ ቢሰነዘር ስለፍቅር ብለን መተው እንጅ ጽንፍ የረገጠ ክብረ ነክ ስድብና ዘለፋ አይበጀንምና በሆደ ሰፊነት በብላቴናው የይቅርታ መንፈስ እናልፈው ዘንድ ምኞቴ ነው 🙏

በመጠረሻም የዛሬው ከሚስ ቀኑ ረዝሞም ቢሆን በሰዓቱ እየተቃረበ ነው። ሰዓቱ ደርሶ መብራት ሳይቆራረጥና ኔትወርክ ሳይጨናነቅ ኢቶሪካ 🎼  ETORIKA 🥁 አዳዲስ ስራዎች በአርምሞ የምንመሰጥ ያድርገን ✋
https://youtube.com/@teddyafroofficial?si=EUaBOsk4TW5Uh6Bx

ኢትዮጵያ ለዘልአለም ትኑር ፣ አሜን🙏

ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዳዲስ እና የሁለተኛ ዙር መራጮች አቅምና ሚና

ግዮን መጽሔት :- በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ የአዳዲስ (ለመጀመሪያ...

በ’ፊንቴክ’ የማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩት ላይ ተጨማሪ ቀጠሮ ተሰጠ

በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ስም በተፈጸመ  የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር...

የጣሊያን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያደረጉት የኢንቨስመንት መጠን 723 ሚሊዮን ዩሮ መድረሱ ተሰማ

ከ20 በላይ የጣሊያን ኩባንያዎች  በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን...

የቴሌግራም ማስጠንቀቂያ

ቴሌግራም (Telegram) ኦፊሴላዊ ያልሆኑ የቴሌግራም መተግበሪያዎችን (Unofficial Apps) በሚጠቀሙ...