ሾልኮ የወጣው ሚስጥራዊው ሰነድ ምንድነው ?

Date:



” ጥቂት ወንጀለኞችን ለማዳን ሲባል በህዝብ ስም መነገድ ይቁም ” – አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ  ፋና ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የተናገሯቸውን ንግግሮች አስመልክቶ የተቃውሞ መግለጫ አውጥተዋል።

በመግለጫው አቶ ጌታቸው ለፋና ቴሌቪዥን የሰጡትን ቃለመጠይቅ ” የህግ ልዕልና ለማረጋገጥ ያለመ ሳይሆን የህዝቡን የትግል ታሪክና ቀጣይነት የሚያጎድፍና የሚያጨልም በቂም በቀል የታጨቀ ነው ” ሲል ገልፆታል። 

” በስልጣን ቆይታቸው የታዩ ወድቀቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ሌላ አካል ሲያላክኩና ከሳሽ ሲሆኑ ሰንብተዋል ” ያለው ፅ/ቤቱ ” ይህ ወደ ሚድያ ፕሮፓጋዳ የወረደ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው ” ብሏል።

የፅ/ቤቱ መግለጫ ፤ አቶ ጌታቸው ህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስመልክቶ በብዙ ጥረት ተጠንቶ ወደ እጃቸው የገባ ኮፒ ያልተደረገ ሰነድ በወቅቱ ተጠያቂነት ሳያረጋግጡ ቀርተው አሁን በማህበራዊ ሚድያ እንዲሰራጭ አደርገዋል ሲል ይከሳል።

” ይህ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ሊያጠቋቸው የፈለጓቸው ግለሰቦች ላይ ብቻ  ያነጣጠረ ሳይሆን ፍትህና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ የሚጎዳ በጥናቱ ተሳትፎ የነበራቸውና አካላትና ቤተሰቦቻቸው ጭምር ለአደጋ የሚያጋልጥ የነውር ነውር ነው ” ሲል በምሬት ወቅሷል።

” የጊዚያዊ  አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት በመሆናቸው ብቻ ያወቁትን ሚስጥር እንደ አንድ የህዝብ ብሄራዊ ጉዳይ እሰከ መጨረሻ መጠበቅ ሲገባቸው ለርካሽ ገበያ ማቅረባቸው ማንነታቸው ያሳየ ተግባር ነው ” ሲል አቶ ጌታቸው ረዳን ወርፉዋቸዋል።

የፕሬዜዳንት ፅ/ቤቱን መግለጫ ተከትለው ወድያውኑ ምላሽ የሰጡት አቶ ጌታቸው ረዳ ” የተጠናው ጥናት ተተንተርሶ ወደ እርምጃ እንደማይገባ ስላወቅኩኝ ወደ ሚመለከተው የበላይ አካል መረጃውን ልኬዋለሁ ” ብለዋል።

ሚንስትሩ ” በጥናት ሰነዱ መሰረት ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ከሚገባ ተጠያቂዎች እንዳንዶቹ ከአገር ወጥተዋል ” ሲሉ ገልጸዋል።

” ‘ ሰው መሸጥ (slave trading in modern parlance  ) ለትግራይ ህዝብ የማይመጥን ወንጀል ነው ‘ የሚል አገላለፅ በፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት በወጣው መግለጫ የለም ” ያሉት አቶ ጌታቸው ” ሰነዱ ግለሰቦችን ከማጥቃት ባለፈ የህግ ልዕልና እንዲረጋገጥ ያለመ ነው ” ሲሉ አብራርተዋል።  

ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ” በጥናት ሰነዱ የተቀመጠው ሃቅ ነው ጥቂት ወንጀለኞች ለማዳን ሲባል በህዝብ ስም መነገድ ይቁም ” ብለዋል።

ሚስጥራዊሰነዱ ምንድነው ?

ከሰሞኑን አንድ ሚስጥራዊ ሰነድ ሾልኮ ወጥቶ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። በማህበራዊ ሚዲያዎችም በርካቶች እየተቀባበሉት ይገኛሉ።

ሚስጥራዊ ሰነዱ ፥ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር (በብዛት ኤርትራውያን በህገ-ወጥ መንገድ ማዘዋወር የሚመለከት) እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ የተጠና ሰነድ ሲሆን በ4 ክፍሎች የተከፋፈሉ 69 ገፆች አሉት።

በሰነዱ በጥናት የተለዩ የወንጀል ተግባራት ፦
– ስልጣን ያለአግባብ በመጠቀም
– በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ በመያዝና በማዘዋወር (መኒ ላውንደሪንግ)
– ሰው ማፈንና መሰወር
– በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ከአገር ወደ አገር ማዘዋወር
– የመንግስት ስራ ምቹ ባልሆነ መንገድ መምራት
– ሃላፊነት ባልተገባ መንገድ በመጠቀም
– ሙስና

መፈፀማቸውን ያረጋግጣል።

በሰነዱ በተጠቀሱ የወንጀል ተግባራት በሰራዊት አመራር ያሉ የነበሩ የጀነራል መዓርግ ካለቸው ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እስከ ቀበሌ አመራር ያሉ አስተዳዳሪዎች ነጋዴዎችና ሌሎች የሚገኙባቸው 231 ተጠርጣሪዎች በስምና አድራሻቸው ተጠቅሷል።

ሰነዱ በህገ-ወጥ መንገድ የተዘዋወሩ ኤርትራውያን ስም የተዘዋወሩበት ቦታና ቀን ፣ ያረፉባቸው ሆቴሎች እንዲሁም ለህገወጥ ዝውውሩ ገንዘብ ገቢ ያደረጉባቸው የባንክ የሂሳብ ቁጥሮች ሰፍረዋል።

የጥናት ሰነዱ የሰው ማስረጃ ፣ የድምፅ ቅጂ፣ እንዲሁም በድብቅ የተቀረፀ ምስል ያካተተ እንደሆነ ይዘረዝራል።

በሰነዱ በቀንደኛ ተጠርጣሪነት ከተጠቀሱት ከፍተኛ መኮንኖች አንዱ የሆኑት ተወልደ ገ/ትንሳኤ (ዕምበብ) በቅርቡ ከአገር መውጣታቸው ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ ከፋና ቴሌቪዥን በነበራቸው ቆይታ ጠቅሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...