በዋለው ችሎት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ እና የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ መካከል የነበረውን የይግባኝ ክስ ፍርድቤቱ ተከሳሹን ነፃ በማለት የክሱ ህደት እንዲቋረጥ ወስኗል።
ቀድሞ ሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ላይ የቀረበዉን የሙስና ክስ ተከትሎ የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 13 አመት ጽኑ እስራት ከተፈረደበት በኋላ፤ ተከሳሹ ያቀረበዉን ይግባኝ የመረመረው የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድቤት በወራት ልዩነት ነጻ ማሰናበቱን የሚታወስ ስሆን፤ ይህንን ውሳኔ በመቃወም የክልሉ ፍትህ ቢሮ (ጠቅላይ አቃቤ ህግ) ይግባኝ ወደ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ወስዶ እንደነበር አይዘነጋም።
