በሰነዶች ማረጋገጫ ንብረት ገዝተው ስም ያላዛወሩ ዜጎች በአስቸኳይ ይዞታቸውን እንዲያስመዘግቡ ተጠየቀ

Date:


 
ቀደም ባሉ ጊዜያት ከሪል እስቴት አልሚዎችም ሆነ ከግለሰቦች ጋር የቤት ወይም የመሬት ግብይት ፈጽመው፣ በሰነዶች ማረጋገጫ ብቻ የያዙና እስካሁን የስመ-ንብረት ዝውውር ያላደረጉ አካላት በአስቸኳይ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ  ጥሪ ቀረበ ።
 
የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ እንደገለጹት፤ ግዢ ፈጽመው የስም ዝውውር ያላደረጉ ወገኖች ለከፍተኛ ጉዳትና ለአደጋ እየተጋለጡ ይገኛሉ።
 
የስመ-ንብረት ዝውውር ዋና ዓላማ አንድ ግለሰብ ያፈራውን ንብረት ለሌላ አካል የሚያስተላልፍበት ሕጋዊ ሥርዓት መሆኑንና የመጨረሻው መዳረሻም የይዞታ ማረጋገጫ (ካርታ) ማግኘት መሆኑን ኃላፊው አስረድተዋል።
 
በመሆኑም ባለንብረቶች መብታቸውን ለማስከበርና ንብረታቸውን ከማንኛውም ሕጋዊ ስጋት ለመጠበቅ ሲሉ፣ ሳይዘገዩ ወደ መሬት ተቋማት በመቅረብ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዜጋዬ ተገድሏል ያለችው ጋና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገባች

አንድ ጋናዊ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ካለው ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ...

«የማይናገረው ልዑል» መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ ነው

ደራሲ መሠረት ክንፈ ኃይሌ ከኦቲዝም ጋር ከሚኖረው ልጇ ልዑል...

በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚደረግ ንግድ በገንዘብ መጠን ተገደበ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚከናወነውን...

(IMF) ከ460 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አፀደቀ

አዳዲስ ብድር በመውሰድ ረገድ ጥንቃቄ እንድታደርግ ኢትዮጵያን ያስጠነቀቀው IMF...