3 ቀን በሀዘን ታስቦ እንዲውል ተወሰነ
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን በግልግል በለስ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ19 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
ዛሬ ግንቦት 10/2017ዓ/ም በግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ከጥዋቱ 3:15 ላይ አንድ ሎቤድ ከላይ ኤክስካባቴር መኪና የጫነ በቴክንክ ብልሽት መስመር ስቶ ሁለገብ ሆቴል ላይ ሻይ ቡና በመጠቀም ላይ ያሉትንና በመንገድ ዳር በግል ስራ ላይ ከነበሩት ሰዎች ላይ በመውጣት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
ከዚህ ቀደምት ብለን በሰራነው ዜገባ የሟቾች ቁጥር 12 መሆንን ብንገልጽም የወደቀው መኪና ከተነሳ በኃላ የሟቾች ቁጥር 19 ደርሷል።
በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወንድ 17 ሴት 2 ድምር 19 ሲሆን ከባድና ቀላል አካል ጉዳት የደረሰባቸው ወንድ 11 ሴት 2 ድምር 13 ሰዎች ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ ሲሆን በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት 55, 500,000 ብር የምሆን ንብረት ላይ ዉድመት መድረሱን የግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኮማንደር ታዬ ጉርሜሳ ገልፀዋል::
በእዚህም ምክንያት የመተከል ዞን አስተዳደር በግልገል በለስ ከተማ በደረሰው ከፍተኛ የመኪና አደጋ ምክንያት ለሶስት ቀናት በሀዘን ታስቦ እንደሚውል አስታውቋል።
