” በተወሰኑ ሳምንታት ግድቡ መጠናቀቁን ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ! ”

Date:

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የ2017 ዓ/ም በጀት አፈጻጸም ሪፖርቱን ዛሬ ይፋ ባደረገበት ወቅት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢ/ር አሸብር ባልቻ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተናግረዋል።

ኢ/ር አሸብር ” የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ሰአት 3400 ሜጋ ዋት ሃይል እያመነጨ ነው ” ያሉ ሲሆን ሲጠናቀቅ በየአመቱ 15,670 ጊዋሰ በላይ የማመንጨት አቅም ይኖረዋል ብለዋል።

በተወሰኑ ሳምንታት ውስጥ መንግስት በሚያወጣው ፕሮግራም ግድቡ መጠናቀቁን ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

ስለ ህዳሴ ግድቡ ዶናልድ ትራንፕ አሜሪካ ለህዳሴ ግድቡ የፋይናንስ ድጋፍ ማድረጓን በተደጋጋሚ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ለፕሬዝዳንቱ ተደጋጋሚ ንግግር ” ሃቁ ያለው እኛ ጋር ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በዝርዝር ምን አሉ ?

” ፕሬዝዳንቱ ብዙ ሊሉ ይችላሉ ሃቁ ያለው እኛ ጋር ነው እንደ ተቋም ብዙ ምላሽ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ሃቅ ስለሆነ።

የግድቡ ግንባታ ፋይናንስ ምንጭ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ፋይናንስ ዶክመንት የሚገኝ ነው ምንም አይነት የውጭ ብድር የለብንም ገንዘቡ የተገኘው ከራስ አቅም ፣በህዝብ እና በመንግስት ድጋፍ ብቻ ነው።

እያንዳንዱ ለግንባታው የሚወጣውን ወጪ በመረጃ ነው የሚያልፈው ለህዝቡ ይፋ ማድረግ ይቻላል።

በዋናነት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለግድቡ ግንባታ ትልቁን ድጋፍ አድርጓል።

ተቋማችን ከንግድ ባንክ የወሰደው ብድርም ለመንግስት በመተላለፉ ግድቡ የተገነባው በመንግስት ነው።

ሁሉም ህዝብ አስተዋጽኦ አድርጓል ነገር ግን ከ90 በመቶ በላይ ወጪ ያደረገው መንግስት ነው።

መረጃ የፈለገ ወደ ተቋሙ በመምጣት አጠቃላይ ወጪውን መመልከት ይችላል።

ብዙ ምላሽ ያልተሰጠው ሃቁ የሚታወቅ በመሆኑ ነው።

ህዳሴ ተጠናቋል የመመረቂያ ቀኑ እና የምረቃ ስነ ስርአቱ ብቻ ነው የቀረው ሳይጠናቀቅ እንኳን ካገኘነው ገቢ ውስጥ ትልቁን ገቢ ያገኘነው በህዳሴ ግድብ ነው።

ይመረቃል ከተባለ በኃላ በግብጽ በኩል እዚህም እዚያም የሚታይ ሩጫ አለ ነገር ግን ምንም ውጤት አያመጣም ግድቡ አልቋል ለምርቃት እየተዘጋጀን ነው።

በተወሰኑ ሳምንታት ውስጥ መንግስት በሚያወጣው ፕሮግራም ግድቡ መጠናቀቁን ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ” ብለዋል ያልው ቲክቫህ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...