በአለም አቀፉ ኢንተርቪዥን ሶንግ ኮንቴስት 2025 ላይ ተሳታፊዋ ድምጻዊት ነጻነት ማነች?

Date:

መስከረም 10/2018 ዓ.ም በሩስያ ዋና ከተማ ሞስኮ “Intervision Song Contest 2025” (ኢንተርቪዥን ሶንግ ኮንቴስት 2025) አሜሪካንን ጨምሮ 23 ሃገሮች የሚሳተፉበት ታላቅ የድምፃዊያን ውድድር ሲካሄድ ወጣቷ ድምጻዊት በባላገሩ በኩል ኢትዮጵያን ትወክላለች።

በጥንታዊቷ ሀረር ከተማ ተወልዳ ያደገችው ነጻነት ገና በለጋ እድሜዋ ነው ወደ ሙዚቃ የተሳበችው።

ከሰባት አመታት በፊት ለህዝብ ያቀረበችው” አባያ”  በተሰኘው የጋሞ ሙዚቃ እንዲሁም እሱን ተከትሎ በተለቀቀው “እና’ በተሰኘው የአማርኛ ዘፈኗ ክህዝብ ጋር በደንብ ተዋውቃለች።

ነጻነት ሱልጣን  ከቅርብ አመታት ወዲህ በሙዚቃ ስራዎቻቸዉ ከፍተኛ አድናቆት እያተረፉ ከሚገኙ ወጣት ኢትዮጵያዊት ድምጻዊያን መካከል አንዷ ናት።

አስካሁን በአማርኛ፣በጋሞ እና በኦሮምኛ ቋንቋዎች  ተወዳጅ ሙዚቃውችን የተጫወተችው ድምጻዊቷ በቀጣይ በአብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሙዚቃዎችን የመስራት ህልም አላት።
የውድድሩ መስፈርት የሚጠይቀውን ብቻ በመመርኮዝ ነፃነት ሱልጣን “ሃላላ” በተሰኘው የኦሮምኛ ዘፈኗ አገራችንን ወክላ ለመጀመርያ ግዜ መስከረም 10 የዉድድር ስራዋን ታቀርባለች።
ነጻነት ሱልጣን  ከቅርብ አመታት ወዲህ በሙዚቃ ስራዎቻቸዉ ከፍተኛ አድናቆት እያተረፉ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ድምጻዊያን መካከል አንዷ ናት።

በተለዋዋጭ የመድረክ አቀራረቧ፣ እና ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ባህላዊ ዜማዎችን ከዘመናዊ የሙዚቃ ስልቶች ጋር በማዋሃድ የምትታወቅ ሲሆን የሀገሯን የቋንቋ ብዝሃነት ለማስተዋወቅ እና ለመጠበቅ ባደረገችው ጥረት በተለይም የኦሮምኛ ቋንቋን በዘመናዊ ሙዚቃዎቿ ውስጥ በማካተት ተወዳጅነትን አትርፋለች።

ተወዳጅነትን ካተረፉ የነፃነት ሱልጣን የሙዚቃ ስራወች መካከል የሚከተሉት  ሙዚቃዎች ይገኙበታል::
“አባያ”  (feat. Sami Go) ( (ነጠላ 2018)
“እና”
“ጉርባዮ” (ነጠላ፣ 2022)
“ኤና” (ነጠላ፣ 2022)
“”ሃላላ” (ነጠላ፣ 2023)
ይገኙበታል::

የውድድሩ መስፈርት የሚጠይቀውን ብቻ በመመርኮዝ ነፃነት ሱልጣን “ሃላላ” በተሰኘው ዘፈኗ አገራችንን ወክላ ለመጀመርያ ግዜ መስከረም 10 የዉድድር ስራዋን ታቀርባለች። በውድድሩ የተሻለ ውጤት እንዲገጥማት የሙዚቃ ስራዋ ወዳጆችና መላ ኢትዮጵያውያን ድጋፋችሁን እንድትሰጧት እንጠይቃለን።

ይህ ዝግጅት የፊታችን ቅዳሜ ምሽት ከ2:00ሰዓት እስከ 5:00ሰዓት በኢትዮጵያ ብቸኛ በሆነው በተባባሪው አዘጋጅ  በባላገሩ ቴሌቪዥን በቀጥታ ይተላለፋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...