የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ
ኢትዮጵያ በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የባህር በር የመፈለግ መብቷን እንደግፋለን ሲሉ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ገለጹ።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ከአል አረቢያ ቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የባህር በር መውጫ የመፈለግ መብቷን እንደግፋን አሉ።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም “የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት በዓለም አቀፍ ህግ ማዕቀፍ ውስጥ አዲስ አይደለም ማንኛውም ሀገር ዓለም አቀፍ ህጎችን እና አህጉራዊ ስምምነቶችን እስካከበረ ድረስ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ሊጠቀምባቸው የሚችላቸው እውቅና ያላቸው ዘዴዎች እና አካሄዶች አሉ” ብለዋል።
ሶማሊያ በእነዚህ ህጋዊ መንገዶች በሰላማዊ እና ድፕሎማሲያዊ መንገድ ከተከተለች ኢትዮጵያ ይህንን ለማሳካት እንደምትችል ተስፋ አለን ሀሳቡን እንደግፋለንም ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ የሶማሊያ አቋም ጽኑ እና ግልጽ ነው ሲሉ አብራርተዋል።
“በቀይ ባህር አዋሳኝ አገሮች፣ የጸጥታና የኢኮኖሚ ፍላጎት ያላቸው አገሮች መረጋጋትን በሚያመጡና ሁሉንም የሚያገለግሉ የጋራ መግባባቶች እንዲፈጠሩ በውይይት፣ በመግባባትና ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
“አለመግባባቶች የሚፈቱት በውይይት፣ በመደራደር እና መግባባትን በመከተል ነው። ይህ የሶማሊያ ጽኑ አቋም ነው”ብለዋል።
ጋዜጣ+
