በአዲስ አበባ ከተማ የወተት እጥረት ማጋጠሙ ተነገረ

Date:

በኢትዮጵያ በዓመት 4.9 ቢሊየን ሊትር የላም ወተት እንደሚመረት መረጃዎች ያመላክታሉ። ይሁን እና የላው የወተት ምርት አቅርቦት በሀገሪቱ ካለው የወተት ፈላጊ ጋር ሲነፃፀር አቅርቦቱ አነስተኛ መሆኑ ይገለፃል።

ምንም እንኳን ከሀገር ሀገር የሚለያይ እና የሚወሰን ቢሆንም የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና ግብርና ድርጅት ፋኦ አንድ ለአቅመ አዳም የደረሰ አዋቂ ሰው ሰውነቱ የሚያስፈልጉትን ማይክሮ ኒውትሬሽን በተሟላ መልኩ እንዲያገኝ በዔመት ከ200 እስከ 250 ሊትር ወተት መጠጣት አለበት ይላል። የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና ግብርና ድርጅት ፋኦ ኢትዮጵያ በዓመት 22 ቢሊዮን ሊትር ወተት እንደሚስፈልጋት ይገልፃል። በ2022 በተደረገ ጥናት የአንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ዓመታዊ የወተት ፍጆታ በአማካይ 20 ሊትር እንደሆነ ያመለክታል። በአሀዝ ከፋኦ እና ከዓለም ጤና ድርጅት መለኪያ በእጅጉ የተራራቀ ከመሆኑ ባለፈ በአፍሪካ በቀንድ ከብት ቁጥር አንደኛ የተባለችው ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ኬንያ እና ኡጋንዳ ዓመታዊ የወተት ፍጆታዋ ያነሰ መሆኑ ይገለፃል።

በወተት እጥረቱ ዙርያ ብስራት ያነጋገራቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከአብይ ፆም መፈታት በኋላ በከተማ ውስጥ  የወተት እጥረት መመልከታቸውን የገለፁ ሲሆን ከእጥረቱ በተጨማሪም የወተት አቅርቦት ባለባቸው ቦታዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያጋጠማቸው መሆኑ ነግረውናል። እንዲሁም ነጋዴዎች በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ከተለያዩ ወተት አቀናባሪ ድርጅቶች በመግዛት ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቡ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን በቂ ወተት ለደንበኞቻቸው ማቅረብ እንዳልቻሉ ነው የገለፁት።

የሆላንድ ዴሪ ምክትል ዋና ስራአስኪያጅ  አቶ ታደሰ ከተማ እንዳሉት የወተት እጥረቱ የተከሰተው ከፋሲካ ፆም በኋላ ያለው ወቅት  እንደሚታወቀው ደረቅ ወቅት ነው የሚባለው አርሶአደሮች መኖ የሚጨርሱበት ወቅት የውሀ ምንጮች የሚደርቁበት እና ሀይላቸው የሚቀንስበትን ወቅት በመሆኑ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከፆሙ በኋላ ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት መኖሩን ገልፀው በመሆኑም ፍላጎት እና አቅርቦቱ አይገናኝም ስለሆነም በዚህ ምክንያት ጊዜያዊ የሆነ የገበያ እጥረት እንዲፈጠር ያደርጋል ሲሉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...