በአዲስ አበባ ከተማ 11 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎትን አላገኙም ተባለ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ በወሊድ የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ 11 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎትን እየፈለጉ ተጠቃሚ መሆን እንዳልቻሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታውቋል።

በቢሮው የተዋልዶ አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ቡድን መሪ ሲስተር አስቴር ለታ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት በአዲስ አበባ መተግበር ከጀመረ ቆየት ቢልም እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ግን ተደራሽ ማድረግ አልተቻለም።

ይህን አገልግሎት ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ በማድረግ የእናቶችንና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ እንደሚረዳ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን የሚያበረክት መሆኑ ተገልጿል።

ቀደም ሲል በተደረጉ ጥናቶች መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ እድሜያቸው ከ15 እስከ 49 የሚሆኑና በመውለድ የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ 11 በመቶ ሴቶች አገልግሎቱን ማግኘት ፈልገው እንደማያገኙ ማረጋገጥ ተችሏል ያሉት ቡድን መሪዋ የወጣት ሴቶች ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችል ተናግረዋል።

ወጣት ሴቶች ስለ ጉዳዮ በቂ እውቀት ስለሌላቸው አገልግሎቱን ላያገኙ እንደሚችሉ የተነገረ ሲሆን እናቶች እንደወለዱ በሚሰጣቸው የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ዙሪያም ፍላጎቶቻቸው የማይሟላበት ሁኔታ መኖሩ ተጠቅሷል።

ይህን ችግር ለመፍታት እናቶች የሚፈልጓቸውን የመድሀኒት አማራጮች በአግባቡ የሚያገኙበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚገባ ሲስተር አስቴር ገልፀው አገልግሎቱን ውጤታማ ለማድረግ በቂ በጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

አገልግሎቱን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የተለያዮ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...