በአዲስ አበባ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር ሊጠናከር ነዉ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋትና የንግድ ስርዓቱን ለመግራት በህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ቁጥጥር እንደሚያጠናክር ገለጸ።

የከተማዋ የታምርት ግብረ ኃይል የ45 ቀናት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የተገመገመ ሲሆን፣ በግምገማው ላይ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ፣ የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና የንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ተገኝተዋል።

ከወረዳ እስከ ማዕከል የሚገኙ የፖሊስ፣ የሠላምና ጸጥታ፣ የደንብ ማስከበርና የንግድ ቢሮ ኃላፊዎች በተሳተፉበት ግምገማ፣ በህገ ወጥ የንግድ ተግባራት ላይ ቁጥጥር በማድረግ 6 ሺህ 123 ነጋዴዎች ላይ የህግ ማስከበር እርምጃ መወሰዱና ከ2 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ወደ ህጋዊ የንግድ ሥርዓት መግባታቸው ተገልጿል።

ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ፣ የህግ ማስከበር ሥራው ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ ሥርዓት ማስገባት በመቻሉ ከ9 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ የከተማ አስተዳደሩ ገቢ እንዳይጠፋ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ድጎማ ማድረጉን ጠቅሰው፣ አቅርቦትን በማሳደግና ህገ ወጥ የንግድ ተግባራትን በመከላከል ለገበያው መረጋጋት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በከተማዋ ከ5 ሺህ በላይ ነጋዴዎች በተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራት ላይ እንደሚሰማሩ ገልጸዋል። ከዘርፍ ውጪ መስራት፣ ያልታደሰ ወይም ያለ ንግድ ፈቃድ መንቀሳቀስ፣ ያለ ደረሰኝ ግብይት ማከናወንና በተጋነነ ዋጋ መሸጥ ከተለዩት ችግሮች መካከል ይገኙበታል። በእነዚህ ላይ የህግ ማስከበር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

የንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው፣ የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ ማረጋጋት ቀጣይነት ያለው ሥራ መሆኑን ጠቅሰው፣ በተለይ የምግብ ሸቀጦች አቅርቦትና ስርጭት በአግባቡ እንዲከናወን ተገቢው ክትትል ሊደረግ እንደሚገባ አመልክተዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጄነራል አስራት ደኔሮ ገበያውን ለማረጋጋት በህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ተገቢው ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባ ገልጸዋል። የቅዳሜና እሁድ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ማበረታታትና ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ጠቅሰው፣ የህግ ማስከበር ሥራው በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል አሳስበዋል።

የክፍለ ከተሞች ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችና ኃላፊዎችም በየክፍለ ከተማቸው የተከናወኑ ሥራዎችን በማቅረብ፣ ከፖሊስ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ያለው ሥራ ውጤታማ መሆኑንና የህብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በዩሮፓ ሊግ አምስተኛ ጨዋታ

በዩሮፓ ሊግ አምስተኛ ጨዋታ ጁቬንቱስ ኦሞኑያ ኒኮስያን 4ለ1 በሆነ...

ኢራን አዲስ ጥቃት ቢፈጸምባት መጠነ-ሰፊ የሚሳኤል አጸፋ ልሰነዝር እንደሚችል አስጠነቀቀች

ኢራን በአሜሪካ ወይም በእስራኤል አዲስ ጥቃት የሚፈጸምባት ከሆነ፣ ከዚህ...

የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎችን በስፖርት ለማሳተፍ የትብብር ውይይት ተካሄደ

የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎች በስፖርት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግና...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አክሱም የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በድጋሚ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ አክሱም ከተማ...