በኢትዮጲያ የሚገኙ የደም ባንኮች ቁጥር 59 ደረሰ

Date:

በተለያዩ ክልሎች ሙሉ አቅም አዳዲስ የደም ባንኮች  እየተገነቡ መሆኑን እና ይህም የበጎ ፍቃድ ደም ለጋሾችን ቁጥር በማሳደግ በደም እጥረት ጉዳት እንዳይደርስ ከማድረጉም ባሻገር  የደም ባንክን ተደራሽነት ይጨምራል ሲሉ የኢትዮጲያ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ታረቀኝ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በኢትዮጲያ ተጨባጭ ሁኔታ በደም ባንክ ተደራሽነት ላይ ወደ ፊት በጥናት እየታየ መሰራት አለበት ያሉት አቶ አለማየሁ በዘንድሮ በጀት አመት በ3 ክልሎች ብቻ በራስ አቅም 10 የደም ባንኮችን ለመገንባት ታቅዶ 6 ያህሉን አጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ተሰርገዋል።

የአሮሚያ ክልል በዘንድሮው የበጀት አመት አራት የደም ባንኮችን ለመገንባት አቅዶ የደምቢ ዶሎና  የሻምቡ የደም ባንኮችን አስመርቆ ለአገልግሎት ማብቃቱን ገልፀው፤በተመሣሣይ የሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት  በክልሉ የሚገኙትን የደም ባንኮች ቁጥር ከ7 ወደ 12 ለማድረስ አቅዶ ፊልቱ፣ ቀብሪደሃርና  ገርቦ የደም ባንኮችን የገነባ ሲሆን የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም የአብአላ ደም ባንክን በመገንባት በክልሉ የሚገኙ የደም ባንኮች ቁጥር 3 ማድረስ ተችሏል።

በአጠቃላይ የደም ባንኮች ግንባታ በሀገሪቱ የሚገኙ የደም ባንኮችን ቁጥር ወደ 59 ማድረሱን የጠቆሙ ሲሆን ይህም በጎ ፍቃድ ደም ለጋሾች በአቅራቢያቸው በመሄድ ደም በመለገስ በደም እጦት ምክንያት ሊጠፉ የሚችሉ ህይወቶችን ለመታደግ አስቻይ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው እና የሀገሪቱ የጤና ሥርዓት መሻሻል አዎንታዊ ሚና እንዳለዉ ተመላክቷል፡፡

#BisratRadio

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...