የዓለም አትሌቲክስ እ.ኤ.አ በመጋቢት 2026 ባወጣው መጽሔት፣ በሦስት ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች የተመዘገቡ አምስት የዓለም የከ20 ዓመት በታች ክብረወሰኖች ከዕድሜ ብቁነት ጋር በተያያዘ ሳይጸድቁ መቅረታቸውን አስታወቀ።
ውድቅ ከተደረጉት ውጤቶች መካከል ሦስቱ በአትሌት ብርቄ ኃይሎም (በ1 ማይል፣ በ1500 ሜትር እና በ5000 ሜትር) የተመዘገቡ ሲሆን፣ ምክንያቱም የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒቲ (AIU) የአትሌቷን የልደት ቀን አጥጋቢ ሆኖ ባለማግኘቱ ነው።
በተመሳሳይ አትሌት መልክናት ውዱ እ.ኤ.አ በ2024 በ3000 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ያስመዘገበችው ፈጣን ሰዓት በዕድሜ መረጃ ጥራት ጉድለት ሳይጸድቅ ቀርቷል።
አምስተኛው ውጤት በአትሌት መዲና ኢሳ በ5000 ሜትር የተመዘገበ ሲሆን፣ ትክክለኛ የልደት ቀኗ ጥቅምት 2002 መሆኑ በመረጋገጡ ውጤቱን በምታስመዘግብበት ወቅት ከዕድሜ ክልሉ በላይ እንደነበረች ተገልጿል።
ይህ ውሳኔ በኢትዮጵያ ወጣት አትሌቶች የዕድሜ ምዝገባ ሂደት ላይ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ አመላካች ሆኗል።
