ትራምፕ አሜሪካ እና ኢራን “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ” ሊወያዩ እንደሚችሉ ተናገሩ

Date:

ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ” ንግግር ሊጀመር እንደሚችል ለኒውዮርክ ፖስት ተናገሩ።

“በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ የሆነ ነገር ሊከሰት ይችላል። እና እኛ የበለጠ ወደዚያ [ፓኪስታን] የመሄድ ዝንባሌ አለን” ማለታቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።

ሁለቱ አገራት የተኩስ አቁም ከደረሱ በኋላ በፓኪስታን ተገናኝተው ለረዥም ሰዓት የተወያዩት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ነበር።

በወቅቱ የአሜሪካን ልዑክ የመሩት ምክትል ፕሬዜዳንቱ ጄዲ ቫንስ ሲሆኑ የኢራን ልዑክ ደግሞ የተመራው በአፈ ጉባዔ ሞሐመድ ባገር ጋሊባፍ ነበር።ነገር ግን ውይይቱ ያለምንም ስምምነት ተቋጭቷል።

ዛሬ የኢራን መገናኛ ብዙኃን በፓኪስታን እና ቴህራን መካከል የመልዕክተት ልውውጥ መኖሩን ዘግበው ከአሜሪካ ጋር ቀጣይ ውይይት ለማድረግ ስምምነት ስለመደረሱ ግን “ምንም መረጃ የለም” ብለው ነበር።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...