አዋሽ ባንክ የ1447ኛውን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ በሸራተን አዲስ ሆቴል ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሃ-ግብር ላይ ለሰባት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የ25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ።
ድጋፉ የተደረገላቸው ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን፣ ዘ ችልድረንስ ኸርት ፈንድ እና እዝነትን ጨምሮ በሕፃናት፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ላይ ለሚሠሩ ተቋማት ነው። ባንኩ ከዚህ በተጨማሪ በ52 የሀገሪቱ ከተሞች ለሚገኙ 2,600 አባወራዎች የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው እንደተናገሩት፤ አዋሽ ባንክ ላለፉት 31 ዓመታት በማዕድ ማጋራት፣ በጤና እና በቤት ግንባታ ዘርፎች ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል።
በአሁኑ ወቅት ባንኩ ከ1,005 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የሪባ-ነፃ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ የሃላል ፋይናንስ ማቅረብ ችሏል።
