በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

Date:

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን በሳይንስ ሙዚየም ኤግዚቢሽን ተከፍቷል

የኤግዘቢሽኑ ከሚያዚያ 15 ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 18 የሚቆይ ሲሆን ዋና አላማው ሻጭ እና ገዢ ማገናኘት፣የግንባታ ግብአት አቅራቢዎች እና ተጠቃማዎችን እንዲገናኙ ለማድረግ፤ የአህጉሪቱን አልሚዎችና ባለሀብቶች በማገናኘት የንግድ ትስስርን ማጠናከር ፣ የሴከተሩ የጥናት ውጤቶችን ማቅረብና ለዘርፉ ችግሮች መፍትሄ ለማስቀመጥ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በዚህ የማህበሩ አባላት ብቻ በተሳትፉበት ልዩ ኤግዚቢሽን ላይ የሪል ስቴት አልሚዎች የተለያዩ ፕሮጀከቶቻቸውን ይዘው የቀረቡ በመሆኑ ቤት እና ሰቅ ፈላጊ ማህበረሰብ አማራጮችን በአንድ ቦታ እንዲያገኝ ሰፊ እድል የሚፈጥር ነው ተብሏል።

በኤግዚብሽኑ መክፈቻ ላይ የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ክብርት ወ/ሮ ሔለን ደበበ ጨምሮ ሌሎች የዘርፉ አካላት ተገኝተዋል::

በዚህ በ4ቱ ቀናት በሚካሄደው ኤክስፖ ከ5000 በላይ ጎብኝዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል::

በተጨማሪም የፋይናንስ ተቋማት፣ የኮንስትራክሽን እና ከዘርፉ ጋር ግንኙነት ያላቸው ድርጅቶች በዝግጅቱ ላይ የሚሳተፉ በመሆኑ ለዘርፉ እድገት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ተነግሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...