ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

Date:

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ በ1.9 ቢሊዮን ብር የገነባውን ሆቴል በይፋ ሥራ ጀምሯል።

ሻለቃ ኃይሌ በምርቃቱ ላይ ባደረገው የምስጋና ንግግር፣ ደብረ ብርሃን የኢንዱስትሪ፣ የሥራ እና የጽናት ከተማ መሆኗን ጠቅሶ፤ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት በመብቃቱ የተሰማውን ጥልቅ ደስታ ገልጿል።

አክሎም “እኛ ኢንቨስት ስናደርግ ትልቁ ዓላማችን የሥራ ዕድል መፍጠርና የአገራችንን ገጽታ መገንባት ነው” ብሏል።

ሆቴሉ ሲገነባ የነበሩ ፈተናዎችን በከተማዋ አስተዳደርና በሕዝቡ ድጋፍ ማለፍ እንደተቻለ የገለጸው ሻለቃ ኃይሌ፤ “ ‘አይቻልም’ የሚል ቃል በኢትዮጵያዊያን መዝገበ ቃላት ውስጥ መኖር የለበትም፤ በትጋትና በሥራ ካሰብንበት እንደርሳለን” ሲል የሥራን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥቷል።

ይህ አዲስ የተመረቀው ሆቴል ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትና የቱሪዝም መዳረሻ እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን፣ ማህበረሰቡም ይህን ታላቅ ሀብት እንዲንከባከበው ጥሪ ቀርቧል።

ሻለቃ ኃይሌ ለፕሮጀክቱ መሳካት ድጋፍ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

ይህ 11ኛው የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት ፕሮጀክት ለአካባቢው ነዋሪዎች ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርና ለከተማዋ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልፁል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...