ስምምነተቱን የተፈራረሙት ትምህርት ሚኒስቴር፣ የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ሀገራት የጋራ ሀብት ልማት ቢሮ (FCDO) እና ብሪቲሽ ካውንስል ናቸው፡፡
ስምመነቱ የተፈረመውም በለንደን ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው የአለም የትምህርት ፎረም 2026 ጎን ለጎን መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል፣ የመምህራን አቅምን ለማጎልበት እና የተማሪዎችን የቋንቋ ክህሎት ለመሳደግ ስምምነቱ ያግዛል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ስምምነቱ በትምህርት ዘርፉ ያለውን ዓለም አቀፍ ትብብር ያጠናከራል፣ ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን የቋንቋ ክህሎት እንዲያዳብሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ መገመቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስረድቷል፡፡
