በእስራኤል ቁልፉን አዛዡን ያጣው ሄዝቦላ

Date:


የሊባኖሱ  ሄዝቦላህ ”ታላቁን ወታደራዊ አዛዥ በእስራኤል ተቀማሁ” አለ።ቤይሩት ላይ እስራኤል በሰነዘረችው የአየር ጥቃት ሃይታም አሊ ታባታባይ መገደላቸውን ሄዝቦላህ አረጋግጧል ።

እስራኤል የፈፀመችው ጥቃት ውጥረቱ እንዲባባስ ያደርጋል እንጂ መፍትሄ አያመጣም በሚልም ሄዝቦላህ ወቅሷል።

ዋና አዛዡ በዳሂየህ ደቡባዊ ቤይሩት ህይዎታቸውን ካጡ አምስት ሰዎች መካከል አንደኛው  ናቸው።

ታላቁ የጦር አዛዥ ተገድለውብኛል ሲል መግለጫ ያወጣው ሄዝቦላህ በጦር ክንፉ ውስጥ ታባታባይ ያላቸውን ማዕረግ በግልፅ አላስቀመጠም።

ከዛሬ ዓመት አንስቶ እስራኤል ከገደለቻቸው ቁልፍ ወታደራዊ አዛዦች መካከል አንደኛው መሆናቸውን ግን ሄዝቦላህ አልካደም።

የእስራኤል ጦር አዛዡን አጥፍተናቸዋል ባለበት ቅፅበት የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ቢሮ ቁልፉ አዛዥ የአየር  ጥቃቱ ዒላማ ሆነዋል የሚል ሀሳብም ማውጣቱ ይታወሳል።

የሄዝቦላህ ከፍተኛ ባለስልጣን ማህሙድ ቅ’ማቲ እስራኤል ቀዩን መስመር አልፋለች ሲሉም አስጠንቅቀዋል ።

የሄዝቦላህ ዓባላት ምላሽ መስጠትን ታሳቢ እያደረጉም ነው ተብሏል።

አሜሪካ እሳቸውን ለጠቆመ አምስት ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ እሽልማለሁ የሚል የይያዝልኝ ትዕዛዝ ቀደም ባሉት ጊዚያት ማውጣቷ አይዘነጋም።

ታባታባይ ከሊባኖሳዊት እናቱና ከኢራናዊ አባቱ በ1960 ዓ.ም ነበር የተወለዱት።

ዘገባው የአልጀዚራ ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...

ከ8 ሺህ በላይ ጥንታዊ የብራና ጽሑፎችን እና ሰነዶችን ወደ ዲጂታል ተቀየሩ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት ከተለያዩ ተቋማት፣...

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...