በጋምቤላ ክልል የመከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ገባ

Date:

በጋምቤላ ክልል ተቀስቅሶ የነበረውን “ ግጭት ” ተከትሎ “ የመከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ወደ ክልሉ መግባቱን ” የክልሉ ፕሬዝዳንት አለሚቱ ኡሙድ ተናግረዋል።

በተለያዩ አቅጣጫዎች ተኩስ እና ግጭቶች እንደተፈጠሩ መዘገቡን ተከትሎ ጥያቄ የቀረበላቸው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሙድ አጭር ማብራሪያን ሰጥተዋል፡፡

ርዕሰ መስተደዳድሯ በክልሉ “ የጸጥታ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር “ አልሸሸጉም። የግጭቱ መንስኤ በተመለከተ ሲናገሩ “ አንድ የፖሊስ አዛዥ በመገደሉ ምክንያት መሆኑን “ ገልፀው አዛዡ ከመገደሉ በፊትም የፀጥታ ችግሮች በአካባቢው ሲፈጠር እንደነበር አስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ ከግድያው በኋላ አካባቢው ሠላም የነበረ ቢሆንም አንዳንድ አከባቢዎች ላይ የተለያዩ የተኩስ ድምጿች ሲሰሙ ነበር ብለዋል።

“ በክልሉ የተነሳው ግጭት አሁን ላይ እየተረጋጋ፣ የከተማው እንቅስቃሴ ሰላማዊ መሆኑንና በከተማው የሚያሰጋ ነገር እንደሌለ “ ርዕሰ መስተዳድሯ ነግረዋታል፡፡


ግጭቱን ለማረጋጋት እና የከተማውን ሠላም ለመጠበቅ ወደ ክልሉ የመከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ  መግባቱንም አስረድተዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ “ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ችግሮች መኖራቸውን “ ገልፀው በቦታው ሠላም ለማስፈን እየተሠራ ነው ብለዋል።

በእርሳቸው ርዕሰ መስተዳድርነት የሚመራው የጋምቤላ ክልል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ በርካታ ያላቸውን ነገር ግን በቁጥር ያልገለጻቸውን ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ከጸጥታ አካላት ውጪ የጦር መሣሪያ የያዘ ግለሰብ ወይም ቡድን አሰፈላጊ ሲል የጠራው እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል፡፡

አዲስ ማለዳ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...