በፍትሕ ዘርፉ የፎረንሲክ ምርመራ ሒደትን ለማጠናከር በትኩረት ይሰራል

Date:

በፍትሕ ዘርፉ የፎረንሲክ ምርመራ ሒደትን ለማጠናከር በትኩረት ይሰራል አሉ የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርአያሥላሴ፡፡

በኢትዮጵያ ሲተገበር የቆየው የአውሮፓ ህብረት የወንጀል ፍትሕ ቴክኒካል ድጋፍ ፕሮግራም ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርአያሥላሴ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኢመስበርገር ተገኝተዋል፡፡

ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የፍትሕ ሥርዓቱን ተደራሽነት ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

የፍትሕ ሥርዓት መጠናከር ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ለማሳካት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

የፍትሕ ሥርዓቱን ተአማኒነት፣ ተደራሽነትና አስተማማኝነት ማረጋገጥ ለብሔራዊ መረጋጋት፣ ለኢኮኖሚ እድገትና ለማህበራዊ ትስስር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አስገንዝበዋል፡፡

የቴክኒካል ድጋፍ ፕሮግራሙ የፍትሕ ዘርፍ ተቋማት ትስስርና አገልግሎት እንዲጠናከር እንዲሁም የፎረንረሲክ ወንጀል ምርመራ ሒደት እንዲሻሻል ጉልህ ሚና መጫወቱን አብራርተዋል፡፡

በፎረንሲክ የታገዘና ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንሚሰራ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በበኩላቸው ÷ በፕሮግራሙ በስልጠና፣ በተሞክሮ መጋራት፣ በአቅም ግንባታ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ውጤት ማስገኘታቸውን አመልክተዋል፡፡

የፍትሕ ሥርዓቱን ለማጠናከር የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ቴዎድሮስ ÷ የአውሮፓ ህብረትና ጂአይዜድ በዘርፉ ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

አምባሳደር ሶፊ ፍሮም÷ የአውሮፓ ህብረት በፍትሕ እና ሌሎች ዘርፍች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

(ኤፍ ኤም ሲ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...