ተኝቶ ያልነቃው የሳውዲ ልዑል አርፏል !!!

Date:

የተሰማው መርዶ…
“================
ብሪታንያ ለንደን በሚገኝ ታዋቂ ወታደራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ትምህርቱን በመከታተል ላይ እያለ ልክ የዛሬ ከ20 ዓመት በፊትበደረሰበት የመኪና አደጋ ከፍተኛ ጉዳት የአልጋ ቁራኛ የሆነው ልዑል ቢሌ ወሊድ ኻሊድ አል ስዑድ ከዚህ አለም ስቃይ መለየቱ እየተነገረ ነው። ልዑል ወሊድ ማረፉ የታወቀው የአባቱ ነው በተባለ የ X አካውንት ላይ በተሰራጨ የሐዘን መግለጫ ነው ። አባቱ ኻሊድ ቢን ጣላል የሚወዱት ልጃቸው ልዑል ወሊድ በተወለደ በ35 ዓመቱ ማረፉን አስታውቀዋል ። ባስተላለፉት ተከታዩን ብለዋል …

” የአላህ ፈቃድ ሆና በመሪር ጥልቅ ሀዘን እና በጥልቅ በሐዘን ልጃችን ልዑል ወሊድ ቢን ኻልድ ቢን ታላል አብድልአዚዝን አርፏል። አላህ በምህረቱ ይጎብኘው።” ሲሉ በህልፈቱ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን አሳውቀዋል ።” በመጨረሻ አባቱ ባስተላለፉት መልዕክት የልዑል ልጃቸው ቀብር በዛሬው እለት እንደሚፈጸም አስረድተዋል። የአባቱ የልዑል ኻልድ ነው በተባለው የግል X ማህበራዊ ሚዲያ ከተሰማው መርዶ ታማኝ አለም አቀፍ የሳውዲ ሚዲያዎች አረጋግጠውታል።

የተኛው የሳውዲ ልዑል ማን ነበር ⁉️

እአአ አፕሪል በ1990 የተወለደው ልዑል ወሊድ ኻልድ ቢን ታላል ቢን ስዑድ የሳውዲ አረቢያ ልዑላን ቤተሰብ አባል ሲሆን ሳውዲን አንድ ያደረጓት የሳውዲ መስራች የቀድሞው ንጉሥ አብልአዚዝ ቢን ስዑድ የልጅ ልጅ ልጅ ነው። አባቱ ኻልድ ቢን ጣላል አል ስዑድ የአሁኑ ንጉስ የንጉሥ ሰልማን ወንድም ልጅ ሲሆኑ ቢሊየኔኑ ልዑል ወሊድ ቢን ጣላል የልዑል ወሊድ አጎት ናቸው።

በልጅነት ዘመኑ ጀምሮ ንቁና ቀልጣፋ ፣ ሰው አክባሪ መልከ መልካሙ ልዑል እንደነበር ቤተሰቦቹ ከዚህ ቀደም ተጠይቀው ከሰጧቸው ቃለ ምልልሶች ተረድቻለሁ ። ወሊድ የ15 ዓመት ለጋ እድሜው የላቀ ወታደራዊ ሳይንስን ተምሮ ሀገሩን በቅንነት የማገልገል ፍላጎት ነበረው ። ይህን ፍላጎቱን የተረዱት ሲበዛ ስልጡን የሆኑ አባቱ ልጃቸውን ወደ ሃገረ ብሪታንያ ለትምህርት ላኩት ። ልዑል ወሊድም ከፍ ባለ ሞራልና ህልሙን ለማሳካት ለንደን በሚገኝ ወታደራዊ ሳንንስ ኮሌጅ ተቀላቀለ ። ልዑል ካልድ በትምህርት አቀባበሉ እጅግ ጎበዝ ተማሪ ከመሆኑ የተነሳ ተስፋ የተጣለበት ቀልጣፋና ንቁ ካዴት ነበር ።በኮሌጅ ትምህርቱ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ትምህርቱን ሲቀጥል መምህራኖቹ እና ወላጆቹ የሚኮሩበት ተማሪ ሆነ ።

ንቁና ትጉሂ ልዑል ህልም መና መቅረት

እአአ በ2005 ዓም በእረፍቱ ወቅት መኪና ሲያሽከረክር የልዑሉን ህይዎት የቀየረ ድንገቸኛ አሰቃቂ የመኪና አደጋ ድንገት ተከሰተ ። አደጋው የሳውዲ ልዑላን ቤተሰቦቹ እስከ ኮሌጁ ተማሪና መምህራኑ ድረስ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ ክስተት ሆነ ። በደረሰበት ከፍተኛ አሰቃቂ አደጋ ልዑል ወሊድ ከአካል ጉዳት አልፎ አዕምሮውን ያሳተውን ጉዳት ያገግም ዘንድ በአለማች አሉ የተባለ ህክምና ቢያገኝም ያ ንቁ ቀልጣፋ ልዑል ተሰናክሎ ቀረ ። ያ አንደበተ ርቱዕ ስልጡን ልዑል ወሊድ አይናገርም አይሰማም አያይም ።ልዑል ወሊድ በአልጋ ላይ ሆኖ በቤተሰቡ እየተጎበኘ በልዩ እንክብካቤ ኖረ ። ነፍሱ ከሥጋው ያልተለየች በድን ሆኖ ላለፉት 20 ዓመታት ከተኛበት መንቃት አልቻለም ።

ከሳውዲ አረቢያ ውጭ ከፍተኛ የህክምና ድጋፍ ተደርጎለት መንቃት አለመቻሉ ሲረጋገጥ ቤተሰቦቹ ልዑሉን ወደ ሳውዲ አረቢያ ሪያድ አስመጡት ። ልዑል ወሊድ ድፍን 20 አመታት ብዙውን እድሜውን ክፍል የገፋው ባለበት ሆኖ ልዩ ከፍተኛ እንክብካቤ በሚያገኝበት በንጉስ ፈይሰል ልዩ ሆስፒታል ተብሎ በሚጠራ ግዙፍ ሳይንስና ምርምር በሚደረግበት የህክምና ተቋም ነው።

⚫️ ልዑሉ የአለም መነገመገሪያም ነበር…

ልዑል አል ወሊድ ደረሰበት አደጋ ወዲህ ለአመታት የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ከተኛበት ባለመንቃቱ አለም መለያ ስም ለጥፎ ይጠራዋል ። ልዑል አል ወሊድ ከሚለው ስሙ ይልቅ ሁሉም የሚያውቀው ” የተኛው የሳውዲ ልዑል” የሚል ስም መለያው ሆኗል ። ” የተኛው የሳውዲ ልዑል” የሚለው የልዑል አል ወሊድ ቅጽል ስም ቀልብ ሳቢነትን ተከትሎ ከአደጋው በኋላ እስከ ቅርብ ጊዜያት ድረስ ተደጋጋሚ የአለም መገናኛ ብዙሃኔ መነጋገሪያ ርዕስም ነበር። ከቅርብ ወራት ወዲህ ” የተኛው የሳውዲ ልዑል” የመንቃት ምልክት አሳዬ የሚል ቀልብ ሳቢ ሰበር በሬ ወለደ መረጃ የዩቲዩብ መነገጃ አድርገውት ተመልክተናል ። የፈጣሪ ድንቅ ታዬ የሚል አንድምታ ትንታኔ እየሰጡ የሶሻል ሚዲያ ወዳጅና የገንዘብ መሰብሰቢያ አድርገውት እንደነበር አይዘነጋም። ከእንግዲህ የልዑሉ መነጋገሪያ መሆን ያከትም ግድ ሆኗል ።

አዎ በደረሰበት አሰቃቂና ከባድ የመኪና አደጋ ላለፉት 20 ዓመታት ሳይነቃ የተኛው ቸሳውዲ ልዑል ቢን ወሊድ ኻሊድ አል ስዑድ በእርግጥም ሥጋው ከነፍሱ ተለይታለች 😢.

ቸርነቱና እና ምህረቱ የማልቅበት ፈጣሪ አምላክ ከቶ አይሳሳትም። ሞትም ድህነትም በእጁ ነው ። የፈቀደውና ያሻውን ያደረገው ፈጣሪ ነፍሱን ለገነተል ፈርዶስ ይበላት 🙏

ነቢዩ ሲራክ
ሐምሌ 13 ቀን 2017 ዓም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...