ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዲሞክራቲክ ሶሻሊስት ሜላት ኪሮስ በኮሎራዶ ምርጫ አንጋፋዋን ዕጩ አሸነፈች

Date:

በዴንቨር ኮሎራዶ በተካሄደው የዴሞክራቲክ ፓርቲ የመጀመሪያ ደረጃ የምርጫ ውድድር፣ የ29 ዓመቷ ትውልደ ኢትዮጵያዊትና ዲሞክራቲክ ሶሻሊስት ሜላት ኪሮስ፣ ለ15 ተከታታይ ዘመናት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩትን ዲያና ደጌትን በከፍተኛ ድምፅ ማሸነፏ ተረጋግጧል።

ይህ ድል በግራ ዘመም (ሌፍትስት) ተራማጅ ፖለቲከኞች በኩል በፓርቲው አንጋፋና ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች ላይ የተመዘገበ የቅርብ ጊዜ ትልቅ ስኬት ተደርጎ ተወስዷል።

78 በመቶ የሚሆነው የምርጫ ድምፅ ተቆጥሮ ሲያበቃ፣ ሜላት ኪሮስ ከተቀናቃኛቸው ደጌት በቅርብ 7 ሺህ የሚበልጥ የድምፅ ብልጫ በመውሰዷ በርካታ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን የምርጫውን ውጤት እንድታሸንፍ ግምት ሰጥተዋል።

በሕፃንነቷ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የተሰደደችውና የቀድሞ የሕግ ባለሙያ የሆነችው ሜላት ኪሮስ፣ በምርጫ ቅስቀሳዋ ወቅት በዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪዎችና በእስራኤል የጋዛ ጦርነት ዙሪያ በወሰደችው ጠንካራ አቋም ሳቢያ ከፍተኛ ትኩረት ስትስብ ቆይታለች።

በተለይም የዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪዎች ለእስራኤል የሚያደርጉትን ድጋፍ በግልጽ በመንቀፍ እና የእስራኤልን እርምጃ “የዘር ማጥፋት” (genocide) ነው በማለት በመኮነን ትታወቃለች። ከዚህ ቀደምም በዚሁ ጉዳይ ላይ የሕግ ተቋማትን የሚተች ጽሑፍ በማኅበራዊ ገጿ ላይ ካጋራች በኋላ፣ ጽሑፉን ለማንሳት ባለመስማማቷ ከሥራዋ መባረሯ ይታወሳል።

ይህ የምርጫ ዲስትሪክት (District) በከፍተኛ ደረጃ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ደጋፊዎች የሚበዙበት በመሆኑ፣ ሜላት በመጪው የኖቬምበር ጠቅላላ ምርጫ በቀላሉ እንደምታሸንፍና የዴንቨር ተወካይ ሆና ወደ ምክር ቤት እንደምትገባ ተገምቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዜጋዬ ተገድሏል ያለችው ጋና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገባች

አንድ ጋናዊ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ካለው ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ...

«የማይናገረው ልዑል» መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ ነው

ደራሲ መሠረት ክንፈ ኃይሌ ከኦቲዝም ጋር ከሚኖረው ልጇ ልዑል...

በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚደረግ ንግድ በገንዘብ መጠን ተገደበ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚከናወነውን...

(IMF) ከ460 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አፀደቀ

አዳዲስ ብድር በመውሰድ ረገድ ጥንቃቄ እንድታደርግ ኢትዮጵያን ያስጠነቀቀው IMF...