“ቻይናን እጎበኛለሁ” ፕሬዚዳንት ትራም

Date:


ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ዓመት(2026) የመጀመሪያዎቹ ወራት ወደ ቤይጂንግ አቀናለሁ አሉ።

የቻይና መንግስት ግብዣ ማቅረቡን ተከትሎ ነው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ2026 የመጀመሪያዎቹ ወራት ቻይናን እጎበኛለሁ ያሉት።

በተጨማሪም ትራምፕ በዚህ ወር የመጨረሻ ሳምንት ገደማ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በደቡብ ኮሪያ እንገናኛለን የሚል ተስፋ ሰንቀዋል።

ፍትሀዊ የንግድ ስምምነት ላይ ለመድረስ ቤይጂንግና ዋሽንግተን በጎ አጋጣሚ ሴዑል ልትፈጥርላቸው እንደምትችልም ተገምቷል።

በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የታሪፍ እሰጥ አገባ መልኩን በለወጠበት ሰዓት መሪዎቹ መገናኘታቸው መልካም ውጤትን ይዞ ይመጣልም ተብሏል።

ቻይና እንደልብ የማይገኙ ማዕድናቷን በተመለከተ የወሰደችውን ዕርምጃ ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ መቶ ፐርሰንት ታሪፍ ከቤይጂንግ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጭማሬ አደርጋለሁ ብለዋል።

በዚህኛው አጋጣሚ መሪዎቹ ከተገናኙ የንግድ ውጥረቱ ቦታ ቦታውን ይይዛል የሚል ዕምነትም ጥለዋል የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች።

በዕርግጥ ዶናልድ ትራምፕና ሺ ጂንፒንግ ከንግድ ነክ ጉዳዮች ባሻገር በወታደራዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘገባው የኤን ቢ ሲ ኒውስ እና የሲ ኤን ኤን ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...