ካናዳን ጨምሮ ወደ የትኛውም የአውሮፓ ሀገር ሕጋዊ ስምሪት የለም

Date:

ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ሕጋዊ የሥራ ስምሪትን ማጠናከር ዋነኛው መፍትሄ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚንስቴር ገለጸ። ካናዳን ጨምሮ ወደየትኛውም የአውሮፓ ሀገር ሕጋዊ ስምሪት አለመኖሩንና ሕብረተሰቡ “የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ እናደርግዎታለን፤ ገንዘብ ላኩ” ከሚሉ አጭበርባሪዎች ራሱን እንዲጠብቅም ሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ አሳስቧል።

በሥራና ክህሎት ሚንስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ በህጋዊ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ዙሪያ ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ቺፍ ኦፍ ሚሺን አቢባቱ ዋኔ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ህጋዊ የሥራ ስምሪቱን ማጠናከር ዋነኛው መፍትሄ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የውጭ አገር የሥራ ስምሪትን አዋጅ አሻሸሎ ወደ ተግባር መግባቱን ተናግረዋል።

የዜጎችን መብት ደህንነት ለማስጠበቅ ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም ሚንስትር ዲኤታው ገልጸዋል።

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ቺፍ ኦፍ ሚሺን አቢባቱ ዋኔ በበኩላቸው፤ ድርጅታቸው በፍልሰት ለስራ ወደ ተለያዩ ሃገራት ለሚሄዱ ሰራተኞች መብትን የሚያሰጠብቁ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቀረጽ የአቅም ግንባታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ድርጅታቸው የሥራና ክህሎት ሚንስቴር ለሚሰራው ሥራ አሰፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደርጉም ቺፍ ኦፍ ሚሺኑ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ካናዳን ጨምሮ ወደየትኛውም የአውሮፓ ሀገር ህጋዊ ስምሪት አለመኖሩንና ሕብረተሰቡ “የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ እናደርግዎታለን፤ ገንዘብ ላኩ” ከሚሉ አጭበርባሪዎች ራሱን እንዲጠብቅ የሥራና ክህሎት ሚንስቴር አሳስቧል።

“ሚኒስቴር መስሪያቤቱም ሆነ ህጋዊ ኤጀንሲዎች ጉዳዮን ለማስጨረስ ምንም ዓይነት ገንዘብ እንዲልኩ አይደውሉም፤ የፅሁፍ መልዕክትም አይልኩም። ከደወሉም ሆነ መልዕክት ከላኩ እነሱ አጭበርባሪዎች ናቸውና ምንም ዓይነት ምላሽ አይስጡ” የሚል ማስጠንቀቂያም አስቀምጧል።

ሕጋዊ የሥራ ስምሪትን በተመለከት ዜጎች የሚንስቴር መሥሪያ ቤቱን ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ እንዲጠቀሙ ማሳሰቡንም ተመልክታለች።

አዲስ_ማለዳ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...