የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ መታሠቢያ ሐውልት ምርቃት

Date:

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ መታሠቢያ ሐውልት ምርቃት እና የቅዱሳን ፓትርያርኮች እና የሊቃነ ጳጳሳት መታሰቢያ የጸሎተ  መርሐ ግብር  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት፣ ሊቀ ጳጳስ፣;ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣  የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ምእመናን እና ቤተሰቦቻቸውና በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ ጸሎተ ወንጌል በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ካህናት መሪነት የተደረገ ሲሆን; ቃለ እግዚአብሔር  በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ካህናት መሪነት በብሔረ ጽጌ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሊቃውንት እና በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ግራ ቀኝ አንሺነት ቀርቧል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቤተክርስቲያናቸውን ከዲቁና  እስከ ፕትርክና በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ አገልግለዋል። ቅዱስነታቸው ወደሀገራቸው ከተመለሱት ጊዜ አንስቶ  በመንበረ ፕትርክናቸው ሆነው ከዚህ ዓለም ድካም እስካረፉበት ቀን ድረስ ስለ ሀገራቸው፣ ስለ ቤተ ክርስቲያንና ስለ ሕዝብ አንድነት በአርምሞ ሲጸልዩ፣ ሲባርኩ ቆይተው የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...