“አላማው ያልታወቀ” ከማንኛውም የውጭ ኃይል ጋር የሚደረግ ግንኙነት “ተቀባይነት የለውም”

Date:

ከማንኛውም የውጭ ኃይል የሚደረግ “አላማው እና ስትራቴጂካዊ ስልቱ ያልታወቀ” ግንኙነት “ተቀባይነት የለውም” ሲል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ገለጸ። ይህን መሰሉ ግንኙነት፤ የትግራይ ክልልን “መንግስት አልባ የሚያደርግ አደገኛ አካሄድ ነው” ሲልም ጊዜያዊ አስተዳደሩ አቋሙን አስታውቋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን ያስታወቀው፤ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በትግራይ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በኩል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው። የትግራይ ህዝብ “ህልውናውን እና ብሔራዊ ጥቅሙን” ለማረጋገጥ “ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እያካሄደ” መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፤ ዋናው ጥያቄው የፕሪቶሪያ ስምምነት “ሳይሸራረፍ ተግባራዊ ይደረግ” የሚል እንደሆነ አስገንዝቧል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በጥቅምት 2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ የተፈረመው የግጭት ማቆም ስምምነት የፈጠረውን ዕድል  ተፈጻሚ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝም ቢሮው አመልክቷል። የትግራይ ህዝብን “ጥቅሞችን እና መብቶች ለማስከበር” እንዲሁም “ከጦርነት ስጋት እንዲጠበቅ ለማድረግ” ጊዜያዊ አስተዳደሩ እየሰራ መሆኑንም ቢሮው አክሏል።

ከፌዴራል መንግስት ጋር ብቻ ሳይሆን ከማንኛውም ኃይል ጋር የሚኖሩ ልዩነቶች ለመፍታት፤ “በሰላማዊ” እና “ህጋዊ መንገድ” “የተቻለውን ሁሉ ጥረት” ማድረግ ተገቢ መሆኑንም መግለጫው አትቷል። ሆኖም “አላማው እና ስትራቴጂካዊ ስልቱ ያልታወቀ”፤ ከማንኛውም የውጭ ኃይል ጋር የሚደረግ ግንኙነት “ተቀባይነት እንደሌለው” ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።  

🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15840/

@EthiopiaInsiderNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...