አሐዱ ባንክ በይፋ ሥራ የጀመረበትን ፫ኛ ዓመት በዓል በማስመልከት ከሳሮ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ክቡሩን የሰው ሕይወት ለመታደግ በአያሌው የሚያግዘውን የደም ልገሳ መርሐ-ግብር አካሒዷል፡፡
በዚህም ባንኩ ካሉት ስድስት ዕሴቶች አንዱ የሆነውን ሰብአዊነት ተግባር ላይ አውሏል፡፡ ለ6ኛ ጊዜ በተካሔደው በዚህ የደም ልገሳ መርሐ-ግብር፤ ከዚህ በፊት ከተደረጉት አምስት የደም ልገሳዎች ከተሰበሰበው ከፍ ያለ የደም መጠን በማስመዝገብ ሪከርድ ሰብሯል፡፡
የደም ልገሳ መርሐ-ግብሩ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት (ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም) ሲከናወን፤ የአሐዱ:ባንክ የሥራ አመራሮች፣ ሠራተኞች፣ የሳሮ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን ኃላፊዎች እና የባንኩ እንደራሴዎች ደም በመለገስ ተሣትፈውበታል፡፡
አሐዱ:ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች!
