አሐዱ:ባንክ በተነሣበት ከብዙዎች ለብዙዎች መርሕ ለብዙዎች ለመድረስ አጠናክሮ በመቀጠል ከኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ጋር በዋናው መሥሪያ ቤት ሐመር አዳራሽ ግንቦት 11/2017 ዓ.ም ስምምነት አደረገ::
የኢንሹራንስ ደንበኞች ለመኪናቸው የሚከፍሉትን ዓመታዊ የአረቦን ክፍያ 22% ብቻ በአሐዱ፡ባንክ በኩል ከቆጠቡ ባንኩ ፋይናንስ በማድረግ ዓመታዊ የኢንሹራንስ ክፍያቸውን እንደሚከፍልላቸው እና በ9 ወራት ጊዜ ውስጥ መክፈል የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን የአሐዱ:ባንክ ተ/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሲሳይ ገብሩ በአፅንኦት ተናግረዋል::
የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽመልስ ገብረ ጊዮርጊስ በበኩላቸው፤ ከተለመደው አሠራር ወጣ ብለን ውጤት እና እድገት ላይ በማተኮር ተባብረን በመሥራት የጋራ ደንበኞቻችንን ለማገልገል አጋርነታችን እጅጉን ወሳኝ ነው በማለት ገልጸዋል::
