አሜሪካ 14 ሀገሮች ላይ የንግድ ታሪፍ እንደምትጥል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ

Date:

ከነሀሴ 1 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል በተባለው በዚህ የንግድ ታሪፍ፤ ሀገሮቹ ከ25 እስከ 40 ከመቶ የሚደርስ ታሪፍ ይጣልባቸዋል ሲሉ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ የቅርብ ወዳጅ የሆኑት ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ በሌሎች 12 ሀገራት ላይ ያነጣጠረው ይህ የንግድ ታሪፍ፤በአሜሪካ ውስጥ ያላቸውን ንግድ እንዲሁም ወደአገራቸው የሚገቡትን የአሜሪካ ምርቶች እንዲያሳድጉ ያለመ ነው ተብሏል።

ትራምፕ ማንኛውንም የአፀፋ እርምጃ የሚወስድ ሀገር ላይ ከዚህ የበለጠ ታሪፍ እንደሚጥሉ በማሳወቅ፤ የንግድ እንቅፋቶችን ላቀለሉ ሀገሮች ከእነዚህ እርምጃዎች እፎይታን እንደሚያገኙ ገልፀዋል።

በአገራቱ ላይ የሚጣለዉ ታሪፍ ከአሜሪካ ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን የገለጹትፕሬዝዳንቱ፤ የንግድ ታሪፉ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል ብለዋል፡፡

ማይናማር እና ካምቦዲያ ከፍተኛውን ማለትም 40 ከመቶ የንግድ ታሪፍ ሲያስተናግዱ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ማሌዥያ፣ካዛኪስታን እና ቱኒዚያ 25 ከመቶ ወይንም ዝቅተኛው የንግድ ታሪፍ እንደሚጣልባቸዉ ተናግረዋል።

ይህ የንግድ ታሪፍ ከተጣለባቸው ሀገራት አብዛኛዎቹ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ውጭ ምርት በመላክ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ያላቸው ሲሆን፤ ከዚህ በፊት 10 በመቶ መሰረታዊ የታክስ ታሪፍ ተጥሎባቸው ነበር ሲል የዘገበዉ አልጀዚራ ነዉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...