አርቲስት ፍቃዱ ከበደ ጳጉሜን ብራንድ አምባሳደር ሆነ

Date:

ጳጉሜን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/ ማሰ/ የህብረት ስራ ማህበር አንጋፋውን አርቲስት ፍቃዱ ከበደን የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ የሾመ ሲሆን ለማህበሩ አባላትና ቆጣቢዎችን ልዩ ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ከሁለት ተቋማት ጋር በይፋ ተፈራርሟል።

የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘላለም ጌታነህ የንግድ መጀመሪያና ማስፋፍያ የቁጠባ ሂደቱ ወደ ንግድ ውስጥ መግባት ለሚፈልጉ ከብድር ባለፈ የዱቤ አገልግሎት ከ5 – 10 በመቶ ቅናሽ ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆኑ 2 ተቋማት ጋርም ስምምነት ፈርሟል።

ግሩንዲንግ ኤሌክትሮኒክስ የኤሌክትሪክ ዕቃ አቅራቢ ተቋም ሲሆን ቴሌቪዥን፣ ልብስ ማጠቢያ፣ ፍሪጅ፣ ኤሲና ሌሎችም በተቋሙ ለገበያ የቀረቡ እቃዎችን በአማካኝ ዋጋ በብድር እንደሚሰጥ አቶ ዳንኤል ነግሮናል።

የኑሮ ጫናን ለመቀነስ አግሪቴክ የዶሮ እርባታና የእንስሳት ተዋጽኦ ውጤቶችን በብድር ለማቅረብ ማሰቡን አቶ ይርጋ አያሌው የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ገልጸዋል።
ያለው ሲሆን ቁጠባና ብድር ተቋሙ ከ 6 ወር እስከ 10 ወር የሚከፈል የብድር አገልግሎት አዘጋጅቷል::

በተጨማሪ የግሩምዲንግ ባለቤት አቶ ዳንኤል ለጵዋግሜ ብድር እና ቁጠባ ተቋም የቤት እቃወች ፍሪጅ የልብስ ማጠብያ ማሽን የውሀ ማጣሪያ ማሽኖች ከ 10/15% የሚደርስ ቅናሽ በማድረግ አብሮ በጋራ ለመስራት ተስማምቷል::

እንዲሁም የአግሪቴክ ሶሊውሽን መስራች የሆኑት አቶ ይርጋ እንደተናገሩት መጪውን በዓል አስመልክቶ እንዲሁም በማንኛውም ጊዜ ዶሮ ለሚፈልጉ ደንበኞች በቅናሽ በማቅረብ ከዛሬ ጀምረው አብረው ለመስራት ተስማምተዋል::

ጷግሜ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበር ሰዎች በፈቃደኝነት ኢኮኖሚአዊ እና ማህበራዊ ችግሮቻቸውን በጋራ ለመፍታት ያቋቋሙት እና የሚአስተዳድሩት እራስ አገዝ ድርጅት ሲሆን የቤት የመኪና ቁጠባ ያለውና ከ 18 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት የተዘጋጀ ቁጠባም እንዳለው በዛሬው መግለጫ ተመልክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...