አሸዋ ቴክኖሎጂ ከ15 በላይ ሶፍትዌሮች ማበልፀጉን አስታወቀ

Date:

በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ግንባር ቀደም ተዋናይ ሆኖ ብቅ ያለው አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ የISO 9ዐዐ1 ሰርቲፋይድ ሲሆን ከ800 በላይ ተቋማትን አሰራር በማቀላጠፍ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ደንበኞችን በማፍራት የላቀ ልምድ ማግኘት ከመቻሉም ባሻገር ከ15 በላይ የደህንነት ምዘና ያለፉና የፈጠራ ባለቤትነትን ያገኘባቸውን ሶፍትዌሮች ማበልፀጉን አስታወቀ።


ከዘልማድ ወደ ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን የሚያሳልጡ ሶፍትዌሮች አበልፅጎ ለተለያዩ የግል እና የመንግስት ተቋማቶች እያቀረበ የሚገኝለት አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ አ.ማ. ከ15 በላይ የደህንነት ምዘና ያለፉና የፈጠራ ባለቤትነት ማረጋገጫ ያገኙ ሶፍትዌሮች ማበልፀግ መቻሉንና ለደንበኞች ለአገልግሎት እንዲዉሉ በማድረግ ላይ መሆኑን የድርጅቱ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳንኤል በቀለ ተናግረዋል።

የድርጅት ሀብት ማቀጃ/ERP/፣ የኢ-ኮሜርስ መተግበሪያ፣ የእቁብ፣ የእድር፣ የሪልእስቴት እና ኮንስትራክሽን፣ የንብረት አስተዳደር ስርዓት፣ የትምህርት አስተዳደር ስርዓት፣ የሰው ኃይል አስተዳደር ስርዓት፣ የሆስፒታል፣ አስተዳደር ስርዓት፣ የንብረት አያያዝ ስርዓት፣ በፍላጎት ላይ የተመሰረቱ ሶፍትዌሮችን፣ ቀላል ፣ ፈጣንና ምቹ የሆነ የዌብሳይት መግንቢያ እና ሌሎችም ስራዎችን በመስራትናየማህበረሰቡን ችግሮች በቴክኖሎጂ መፍታት የሚችሉ እንደሆኑም ተብራርቷል።

ከ1,600 በላይ ባለአክሲዮኖች፣ ከ325 ሚሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ካፒታል እና ከ200 በላይ ብቁ ባለሙያዎችን በመያዝ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የላቀ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ. አኦላይን ሾፒንግ’ ስማርት ኢ.አር.ፒ ሲስተም፣ አሸዋ ክላውድ፣ ኢንተርፕራይዝ ሶፍትዌር ትግበራ እና ግንባታ፣ ሞባይልአፕልኬሽን ግንባታ፣ ዌብሳይት ፖርታል ግንባታ፣አሸዋ ክላውድ ኮንፒውቲንግ (Ashewa Cloud computing) ‘የኳሊት አሹራንስ’ ሴኩሪቲ ቴስቲንግ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን እያቀረበ የሚገኝ ሀገር በቀል ኩባንያ ነዉ፡፡

የበርካታ መንግስታዊ እና የግል ድርጅቶችን ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂ ስራዎችን በመስራት ላይ መገኘቱ የተብራራ ሲሆን ከተመሰረተ በአጭር ጊዜ ስኬታማ ለመሆን መቻሉንም የድርጅቱ ሃላፊዎች ነግረዉናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...