ስምምንቱ ዓባይ ባንክ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ምቹ እንዲሁም አለም አቀፍ እውቅና ያላቸው የክፍያ መፍትሄዎችን ለደንበኞቹ ማቅረብ የሚያስችለው እንደሆነ ተገልጿል።
ከዛ ባለፈም የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን ከመግታት እንዲሁም ኢትዮጵያውያን በዲጂታል ኢኮኖሚው እንዲሳተፉ ከማስቻል አንፃር ለሚደረገው እንቅስቃሴም ጥቅም እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
በፈርማ ሥነሥርዓቱ ላይ የአባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ ባንኩ የሀገር ውስጥ እንቅስቃሴን ዲጂታል ከማድረግ አንፃር ውጤታማ መሆናቸውንና የዛሬው ስምምነት ደግሞ አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለማቅረብና ለማስፋፋት ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል።
የዓባይ ባንክን በሀገር ውስጥ ሰፈ ተደራሽነት ከቪዛ ዓለም አቀፍ ልምድ ጋር በማቀናጀት በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ዲጂታል ከፍያ የሚደረገውን ሽግግር ለማፋጠን እና የሀገሪቱን ዘመናዊ እና ከጥሬ ገንዘብ ዝውውር ነፃ የሆነ ኢኮኖሚ ራዕይ በመደገፍ የሚፈለገውን ስኬት ለማስመዝገብ ስምምነቱ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡
