አዋሽ ባንክ እና የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

Date:

አዋሽ ባንክ እና የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ፣ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት በዛሬው እለት ማለትም ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም፣ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡

በፊርማው ሥነ ሥርዓት ላይ፣ የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው እንደገለጹት፣ ባንኩ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነውን ግብርና ፋይናንስ ለማድረግና ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀው፣ ለዚህም በግብርናው መስክ ከተሰማራው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት በማድረጉ ኩራት ይሰማዋል ብለዋል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም በበኩላቸው፣ ስምምነቱ ኮርፖሬሽኑ ከባንኩ በሚያገኘው ብድር የእርሻ መሣሪያዎችን፣ እንዲሁም የግብርና ግብዓቶች ማጓጓዣ፣ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ከውጭ በመግዛትና በመገጣጠም ለአርሶ አደሮች፣ ለባለሃብቶች እና በዘርፉ ለተሰማሩ ሌሎች ተጠቃሚዎች በስፋት ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

አዋሽ ባንክ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነት በማድረግ በትብብር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...