አቶ ዘካርያስ ከጥር 5 ቀን 2018 ጀምሮ አዲሱን ኃላፊነታቸውን ተረክበው ሥራ መጀመራቸውን የምክር ቤቱ ቦርድ አስታውቋል።
አቶ ዘካሪያስ ላለፉት 9 አመታት በአዲስ ቻምበር የንግድ ድጋፍ አገልግሎት እና የአድቮኬሲ ዘርፍን በምክትል ዋና ፀሐፊነት ሲመሩ ነበር።
አቶ ዘካርያስ አሰፋ ከእንግሊዙ ማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ በሰው ኃይል አስተዳደር የማስተርስ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን፣ ወደ አዲስ ቻምበር ከመቀላቀላቸው በፊትም የኢትዮጵያ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩትን በዋና ዳይሬክተርነት እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ላይ ደግሞ የሥልጠና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር በመሆን ማገልገላቸው ተገልጿል።
በ1939 ዓ.ም የተመሠረተው አዲስ ቻምበር፣ የንግድ ማኅበረሰቡ ድምፅ በመሆን በንግዱ ማህበረሰብና በመንግሥት መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል የ79 አመት አንጋፋ ተቋም ነው።
