ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኢኮኖሚ መሪ እንድትሆን እስራኤል ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች

Date:

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር በኢኮኖሚና በሉዓላዊነት የጠነከረች መሪ ሀገር እንድትሆን እስራኤል ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ።

አምባሳደሩ የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከፌስቡክ ተከታዮቻቸው ጋር ባደረጉት የቀጥታ ውይይት እንደተናገሩት፣ የሁለቱ ሀገራት የ70 ዓመት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በጥልቅ ታሪክ፣ ባህልና ሃይማኖት ላይ የተመሰረተ ነው።

ሁለቱም ሀገራት የራሳቸው ልዩ የቀን መቁጠሪያ የሚከተሉ በመሆናቸውና የአዲስ ዓመት በዓላቸው በአንድ ቀን መዋሉ ልዩ ቁርኝታቸውን እንደሚያንጸባርቅ በመጠቆም፣ እስራኤል የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ፣ የፈጠራና የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ እየሰራች መሆኑን አስታውቀዋል።

የሁለቱ ሀገራት ትብብር በዓለም አቀፍ መድረኮች በመደጋገፍ፣ በመንግስታት ትብብርና በግል ኢንቨስትመንት ማስፋፋት ላይ ያተኮረ መሆኑን አምባሳደሩ አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅት ከ100 በላይ የእስራኤል ባለሀብቶች በግብርና፣ ቴክኖሎጂና ሕክምና ዘርፎች በኢትዮጵያ የተሰማሩ ሲሆን፣ በተለይም በነጻ የልብና የዓይን ቀዶ ጥገና ሕክምናዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቴል አቪቭ የሚያደርገው በረራ የንግድ፣ የቱሪዝም እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ይበልጥ እያጠናከረው እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...