International Military Sports Council በ 1948 መቀመጫውን ብራሰልስ ቤልጀም በማድረግ ነው የተመሰረተው።
ከአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በመቀጠል ሁለተኛው ግዙፉ የስፖርት ካውንስል ነው።
ኢትዮጵያ ከ160 አባል ሀገራት መካከል አንዷ መሆን ችላለች።በዚህ ካውንስል ኤርትራ እና ሰሜን ኮሪያም አባል ሀገራቶች ናቸው።
ይህ ካውንስል በአመት ከ 20 በላይ ትልልቅ ውድድሮችን ያዘጋጃል፣ስፖርተኞችን በአካል እና በአዕምሮ ያደጉ ያደርጋል።
ከዚህ በኋላ ካውንስሉ በሚያዘጋጀው military world games እና military world championship ኢትዮጵያ ብቁ ተወዳዳሪዎችን በየአመቱ አዘጋጅታ ወደ ውድድር ትገባለች ተብሏል።
ወዳጅነት በስፖርት (friendship with sport ) በሚል መርህ ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ ይህ ካውንስል በአለም ላይ ሰላም እና ስፖርትን እየሰበከ ቆይቷል።
ካውንስሉ ለ140 አባል አገሮች የጦር ኃይሎቻቸው የCISM አላማን በማስረፅ የስፖርት እንቅስቃሴን እና የአካል ማጎልመሻ ትምህርትን የአለምን ሰላም ለማስፈን እንደ ድልድይ እየተጠቀ ይገኛል።
