ኢትዮጵያ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤን ልታስተናግድ ነው

Date:

ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (Africa Social Media Influencers Summit & ASMIS) በአዲስ አበባ እንደምታስተናግድ ተበሰረ።

​የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ (POA) እና ኤ.ጂ.ኤ ቴክ (AGA-Tech) በጋራ በሰጡት መግለጫ የጉባኤውን ዝርዝር ይፋ አድርገዋል።

​ የጉባኤው መርሃ-ግብር

​ቀን፦ ግንቦት 7 እና 8 ቀን 2026 (እ.አ.አ)
​ቦታ፦ አዲስ አበባ፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ
​መሪ ቃል፦ & ለተሻለች አፍሪካ&

​የጉባኤው ዋና ዋና ዓላማዎች

​የጋራ መድረክ መፍጠር፦ የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ድምፆችን ከመገናኛ ብዙኅን፣ ከፖሊሲ አውጪዎችና ከንግድ መሪዎች ጋር ማገናኘት።

​ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ቴክኖሎጂ፦ በፈጣን ዕድገት ላይ ባለው AI እና በዲጂታል ይዘት ፈጠራ ዙሪያ ልምድ መለዋወጥ።

​የአፍሪካን ታሪክ መግለጥ፦ ስለ አህጉሪቱ መፃኢ ተስፋና ታሪክ ጥራት ያላቸው የይዘት ሥራዎችን ለማስተጋባት አቅም መፍጠር።
​ቢዝነስ እና ትስስር፦ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ከታላላቅ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የንግድ ድርጅቶች ጋር ማገናኘት።

​በአህጉሪቱና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ከ200 በላይ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በጉባኤው ላይ ይታደማሉ።

እንዴት መሳተፍ ትችላላችሁ
​የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ባዩሽ ማሞ እንደገለጹት፣ የጉባኤው ይፋዊ ምዝገባ በቅርቡ ይጀመራል። የይዘት ፈጣሪዎችና ፍላጎቱ ያላቸው አካላት የሚከተለውን ድረ-ገጽ በመከታተል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፦
www.asmis.org

​ይህ ጉባኤ አዲስ አበባን የአፍሪካ የዲጂታል ዲፕሎማሲ ማዕከል ከማድረጉም በላይ፣ የአህጉሪቱን የፈጠራ አቅም ለዓለም ለማሳየት ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...