ኢትዮጵያ ያለው የሎጅስቲክስ ዘርፍ እጅግ በጣም ዝቅተኛና ኋላቀር መሆኑ ተገለጸ

Date:

ኢትዮጵያ የራሷ የባህር ወደብ የሌላት መሆኑ የሎጅስቲክሱ ዘርፍ እጅግ በጣም ዝቅተኛና ኋላቀር ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ፍሬት ፎርዋርደርስ ኤንድ ሺፒንግ ኤጀንትስ አሶሴሽን ከብሪታኒያ ዓለም አቀፍ የጭነት አስተላላፊዎች ማኅበር ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረሙበት ወቅት ነው፡፡

ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ በኢትዮጵያ ያለው የሎጅስቲክስ ዘርፍ ከዓለም ሁኔታ አንጻር ሲወዳደር እጅግ በጣም ዝቅተኛና ኋላቀር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የጋራ መግባቢያ ሰነዱ መ’ፈረሙ የኢትዮጵያን የሎጅስቲክስ ዘርፍ ዘመናዊና ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችል እርምጃ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ከተቀረው ዓለም ጋር ሲወዳደር እጅግ በጣም ዝቅተኛና ኋላቀር ነው ለተባለው የኢትዮጵያ የሎጅስቲክስ ዘርፍ ከባህር ወደብ አለመኖር በተጨማሪ በቂና ዘመናዊ የመሠረተ ልማት አውታሮች አለመኖራቸው፣ ለዘርፉ የሚመጥን የተቀናጀ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አለመኖሩ፣ እንዲሁም በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረትና ሌሎችም አበይት ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ፍሬት ፎርዋርደርስ ኤንድ ሺፒንግ ኤጀንትስ አሶሴሽን ከብሪታኒያ ዓለም አቀፍ የጭነት አስተላላፊዎች ማኅበር ጋር የተፈራረመው ስምምነት የሎጅስቲክስ ዘርፉን ለማዘመን ከፍተኛ አገራዊ ፋይዳ እንዳለውም በመድረኩ ተገልጿል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...