ኤርትራ የነበሩት የሳዑዲ ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

Date:

ከሳምንት በፊት ኤርትራ የነበሩት የሳዑዲ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አልኬሬጂ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ጋር በአዲስ አበባ ተገናኝተው ተወያዩ።

ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ሰኞ የካቲት 16/2018 ዓ.ም. ተገናኝተው በቀጠናዊ ሰላም እና ሁለቱን አገራት በሚመለከቱ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተገልጿል።

የሳዑዲ አረቢያው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሳምንት በፊት በአሥመራ ተገኝተው ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በቀይ ባሕር እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተው ነበር።

የሳዑዲው ውጭ ጉዳይ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ጋር በተገናኙበት ወቅት በቀይ ባሕር ዳርቻ አገራቱ በሰላም እና በደኅንነት ጉዳዮች ላይ በሚኖራቸው አስተዋጽኦ ላይ ተነጋግረዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት የሳዑዲ አረቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሐን ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ እንዲሁም ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው እንደነበር ይታወሳል።

በወቅቱ የሳዑዲው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር በቁልፍ ዘርፎች ላይ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር እንዲሁም የሁለቱም አገራት ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በሚኖራቸው ትብብር ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጾ ነበር።

የሳዑዲ ምክትል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አልኬሬጂ ለሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጥቅም ላይ በተመሰረቱ ቀጣናዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ምክክር ማድረጋቸው ተገልጿል።

ከሳምንታት በፊት የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ሳዑዲ አረቢያ በመጓዝ ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር መገናኘታቸው ይታወሳል።

ከሳምንት በፊት አሥመራ የነበሩት የሳዑዲው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ አዲስ አበባ የመጡት በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ግጭት ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት ባየለበት ጊዜ ነው።

BBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ንባብ ለህይወት!” ታላቅ የንባብ ሳምንት እና የመጻሕፍት አውደ ርዕይ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የንባብ ለህይወት...

በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ

በኢትዮጵያ ከ10 ሚልዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ እና ከ2...

የቶዮታ ኮሮላ መኪና በኤሌክትሪክ ሊመጣ ነዉ

የዓለማችን ግዙፍ የመኪና አምራች የሆነው ቶዮታ፤ እንደ ቴስላ እና...

ኢራንን ለመምታት የዩናይትድ ስቴትስ ጄቶች ከምድሯ ይነሱ እንደነበር እሥራኤል ይፋ አደረገች

የእሥራኤል መከላከያ ሚንሥትር እሥራኤል ካትስ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ጄቶች...