ከምዝገባ ካርድ ባሻገር፦ ለነገው ድምፅ የዛሬው ጥንቃቄ

Date:



ግዮን መጽሔት :- የምርጫ ካርድዎን በእጅዎ ይዘዋል? እንኳን ደስ አለዎት! የዜግነት መብትዎን ለመጠቀምና በአገራችን ዕጣ ፈንታ ላይ ለመወሰን የመጀመሪያውንና ወሳኙን እርምጃ ተራምደዋል፡፡ ይሁን እንጂ የምርጫ ካርድ መያዝ በራሱ ግብ አይደለም፤ ይልቁንም ትልቅ አገራዊ ኃላፊነት መሸከም እንጂ፡፡

አሁን ያለንበት ወቅት የጩኸትና የቅስቀሳ ሳይሆን፣ የጥንቃቄና የጥልቅ ምርመራ ጊዜ ነው፡፡ መራጭ መሆን ማለት ዝም ብሎ ድምፅን ወደ ሳጥን ውስጥ መክተት አይደለም፡፡ መራጭ መሆን ማለት እንደ አገር የሚቀጥሉትን ዓመታት የሚመራን ‹ሥራ አስኪያጅ› የመቅጠር ያህል ጥንቃቄ የሚጠይቅ የውሳኔ ሂደት ነው፡፡

የወጣቶችና የባህል ልማት ፋውንዴሽን (YCDF)፣ ወጣቱና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምዝገባው ማግስት ወደ ምርጫው ሳጥን ከመጓዙ በፊት ሊያደርጋቸው በሚገቡ ወሳኝ ‘የቤት ሥራዎች’ ላይ የሚከተለውን ትንታኔ ያቀርባል፡፡

  1. የምርጫ ቃል ወይንስ ተግባራዊ ዕቅድ?

  2. የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ዕጩዎች ማራኪ ቃላትን፣ ተስፋ ሰጪ ንግግሮችንና ታላላቅ ቃል ኪዳኖችን የሚያዥካኩበት ወቅት ነው፡፡ እኛ መራጮች ግን ከቃላቱ ጀርባ ያለውን እውነታ መመርመር ይኖርብናል፡፡
  • ተግባራዊነትን መመዘን፦ አንድ ዕጩ ‹‹ይህንን አደርጋለሁ›› ሲል፣ ‹‹እንዴት?›› ብሎ መጠየቅ የንቁ ዜጋ መገለጫ ነው፡፡ ‹‹ሥራ እፈጥራለሁ›› የሚል ቃል ኪዳን ካለ፣ በምን ዓይነት ፖሊሲ? ከየት በሚገኝ በጀት? እና በምን ያህል ጊዜ? የሚሉትን ጥያቄዎች በሰክነ መንፈስ ልንመዝን ይገባል፡፡
  • ከስሜታዊነት መውጣት፦ ፖለቲካዊ ንግግሮች ስሜታችንን ሊኮረኩሩ፣ ብሔራዊ ወይንም አካባቢያዊ ስሜታችንን ሊቀሰቅሱ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ድምፅ የሚሰጠው ለስሜት ሳይሆን ለዕውቀትና ለውጤት መሆን አለበት፡፡ ዛሬ በስሜት የምንሰጠው ድምፅ ነገ ዋጋ እንዳያስከፍለን፣ የምክንያታዊነት ሚዛናችንን ማጥበቅ ይኖርብናል፡፡
  1. ያለፈ ታሪክ (Track Record) እንደ መስተዋት

  2. አንድን ዕጩ ለመመዘን ከሁሉ የተሻለው መንገድ ያለፈውን ታሪኩን ማየት ነው። ‹‹የቆመበትን የሚያውቅ የሚሄድበትን አይስትም›› እንዲሉ፣ ዕጩው ቀደም ሲል በነበሩት የኃላፊነት ቦታዎች ምን ሠርቷል? የሚለውን መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡
  • ለሕዝብ አገልግሎት ያለው ታማኝነት፦ ዕጩው ከዚህ ቀደም በማኅበራዊ አገልግሎት፣ በሙያዊ መስክ ወይንም በፖለቲካ ተሳትፎው ለሕዝብ ጥቅም ቅድሚያ ሰጥቷል? ወይንስ የግልና የቡድን ጥቅምን ሲያሳድድ የነበረ ነው?
  • የቃላትና የተግባር አንድነት፦ ቀደም ሲል የገባቸውን ቃል ኪዳኖች ምን ያህሉን አክብሯል? የሚለውን ማየት የዕጩውን ተዓማኒነት ለመለካት ይረዳል፡፡ በትላንት ታሪኩ ያልተፈተነ ዕጩ፣ የነገን አደራ ሊሸከም አይችልም፡፡
  • የዚህን ፁሑፍ ቀጣይ ክፍል ነገ ይጠብቁን

ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው በወጣቶች እና ባህል ልማት ፋውንዴሽን (Youth and Cultural Development Foun dation – YCDF) ከአውሮፓ የምርጫ ድጋፍ ማዕከል (ECES)  ጋር በመተባበር ነው።

የወጣቶች እና ባህል ልማት ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ውስጥ የወጣቶችን ሁለንተናዊ አቅም በመገንባት፣ ባህላዊ እሴቶችን በማሳደግ፣ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን በማስፋፋት እና የወጣቶችን ንቁ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ በማጎልበት ላይ በትኩረት የሚሠራ ገለልተኛ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ወጣቶች በሀገር ግንባታ ሒደት ውስጥ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ግንዛቤ በመፍጠርና አቅማቸውን በማጎልበት የላቀ አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ነፃነት ከዳቦ ይበልጣል!

የአርበኞች አደራና የትውልዱ ዕዳ! ከሣልሳዊት ባይነሳኝ ግዮን መጽሔት :- ከዓለም ድንቅ...

በኢትዮጵያ የዲጂታል ኦቲዝም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለፀ

ልጆች ረጅም ሰዓት በስልክና በቪዲዮ ጌሞች ላይ ማሳለፋቸው፣ መናገር...

ፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ በቻይና ውይይት ያደርጋሉ 

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ወደ ቻይና የሚያደርጉትን መጪ ጉብኝት አስመልክቶ የክሬምሊን...

በጤና አገልግሎት ማስታወቂያዎች ላይ የሕመምተኞችን ምስክርነት መጠቀም ተከለከለ

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ...