ከአክሱም እስከ አሜሪካ የመንትዮቹ የህክምና ጉዞ!

Date:

ተጣብቀው ተወልደው ለሁለት ዓመታት ያህል አንድ ላይ የቆዩት ተአምረኞቹ መንትዮች ህያብ እና ወህብቶ በአሜሪካ በሚገኘው ሴይንት ሉዊስ ሆስፒታል በተደረገላቸው እጅግ ውስብስብ ቀዶ ህክምና በስኬት መለያየታቸው ተበሰረ።

ታሪኩ የሚጀምረው መጋቢት 2016 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ኮንፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው።

ህያብ እና ወህብቶ ተጣብቀው ወደዚህች ዓለም ሲቀላቀሉ ቤተሰቦቻቸው በደስታ እና በስጋት መካከል ነበሩ።

ሆስፒታሉ ለ8 ወራት ያህል ልዩ እንክብካቤ ሲያደርግላቸው የቆየ ቢሆንም የቤተሰቦቻቸው የኢኮኖሚ አቅም ግን ለቀጣዩ ከባድ ህክምና ፈታኝ ነበር። የመንትዮቹ ቤተሰቦች በኢኮኖሚ አልደረጁም።

በመቐለ የሚገኘው ሎላ የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከል የህፃናቱን ሁኔታ ተረድቶ ኃላፊነቱን በመውሰድ ተጨማሪ የህክምና ዕድሎችን መፈለግ ጀመረ።

ጥረቱም ፍሬ አፍርቶ በአሜሪካ ነዋሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ባደረጉት ከፍተኛ እገዛ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ህፃናቱ ወደ አሜሪካ ሚዙሪ ግዛት አቀኑ።

ባለፉት ወራት ህፃናቱ በሴይንት ሉዊስ ሆስፒታል አራት ተከታታይ እና ከባድ የቀዶ ህክምናዎችን አልፈዋል።

በመጨረሻም የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም አምስተኛው እና ወሳኙ የቀዶ ህክምና ስራ ተከናወነ።

በዚህም ለሁለት ዓመታት ተጣብቀው የነበሩት ህፃናት በሰላም ተለያዩ።

የህፃናቱ አባት አቶ ሙኡዝ አብርሃ ከአሜሪካ ሆስፒታል ባስተላለፉት መልእክት፣ ” ህክምናው ተሳክቶ ህያብና ወህብቶ በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ” በማለት አብስረዋል።

ይህ ስኬት የህክምና ጥበብ ውጤት ብቻ ሳይሆን የሰው ልጆች ርህራሄ እና ትብብር ምን ያህል ተአምር እንደሚሰራ የታየበት ደማቅ ታሪክ ነው።

ቲክቫህ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሕገ መንግሥቱ መገንጠልን ይፈቅዳል ፤ ሕዝቡ ደግሞ ኢትዮጵያ እንድትቀጥል ዋጋ ይከፍላል”

አቶ ፍሬሕይወት ሳሙኤል(የ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች›› መጽሐፍ ደራሲ) ግዮን መጽሔት :-...

ባለሙያ ባልሆኑ ግለሰቦች የሚሰራጭ የተዛባ መረጃ በታካሚዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነዉ

የሳይካትሪስት የሙያ ፈቃድና ሥልጠና የሌላቸው ግለሰቦች በተለያዩ መገናኛ...

የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የ1.2 ቢሊዮን ዩሮ ስምምነት ሊፈራረሙ ነው

በአውሮፓ ህብረት እና በኢትዮጵያ መካከል በሚካሄደው የንግድ ፎረም መክፈቻ...

የአዳዲስ እና የሁለተኛ ዙር መራጮች አቅምና ሚና

ግዮን መጽሔት :- በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ የአዳዲስ (ለመጀመሪያ...