” ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ ይመለሳሉ ” – ፅ/ቤቱ

Date:



ላለፉት 12 ቀናት በስራ ማቆም አድማ የቆዩት የመቐለ ዳኞች ስራ ለመጀመር መግባባት ላይ መደረሳቸው ተነግሯል።

ዳኞቹ ያቀረቡት የደህንነት ስጋት ጥያቄ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተለው በተደረሰው ስምምነት ምክንያት ነው ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ የወሰኑት።  

የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ” ዳኞቹ ያለባቸው የድህንነት ስጋት በማስመልከት ከፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እና ከፍትህ አካላት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል ” ብሏል።

” በውይይቱ በዳኞቹ ላይ ያንዣበበው የደህንነት ስጋት በጥልቀት ተዳሷል ፤ ችግሩን ከስሩ በመረዳት ለመፍትሄው ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ” ሲል ገልጿል።  

” የደህንነት ስጋቱ በዘላቂነት ለመፍታት የአጭርና የረጅም ጊዜ  የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። በተደረሰው መግባባት መሰረት የመቐለ ሰባቱ ክፍለ ከተማ ፍርድ ቤቶች ከዛሬ ግንቦት 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ ይመለሳሉ ” ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...